ራስ ቴአትር ታሪካዊ ይዘት አለው የተባለውን “ወህኒ አምባ” ቲያትር ግንቦት 16 ሊያስመርቅ መሆኑ ገለጸ።
#Ethiopia | በአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት የራስ ቴአትር ክፍል በታሪካዊ ይዘቱና በዝግጅት መጠኑ ታላቅ የተባለለትን አዲስ ቲያትር ሊያስመርቅ ነው።
ይህ አዲስ ቲያትር “ወህኒ አምባ” የተሰኘ ሲሆን በቀጣዩ ሳምንት ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚያስመርቅ አስታወቀ።
በደራሲ መልካሙ ዘርይሁን ተጽፎ በአዘጋጅ ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ ወደ መድረክ የመጣው “ወህኒ አምባ” ታሪካዊ ድራማ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት የሕፃናትና ወጣቶች ቴአትር ቤት አዳራሽ ይካሄዳል።
በምረቃው ፕሮግራም ላይ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው ታዋቂ የኪነ-ጥበብ ሰዎችና የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚታደሙ ታውቋል።
የዚህ ቲያትር ዋና ዓላማ የሀገሪቱን የጥበብ ዘርፍ ለማሳደግና የታሪክ ድርሳናትን በኪነ-ጥበብ አማካኝነት ለትውልድ ለማስተላለፍ እንደሆነ ተገልጿል።
የቴአትር ቤቱ አስተዳደር ለሥራው መሳካት ቀጣይነት ያለው ትብብርና ድጋፍ ለሚያደርጉ አካላት ሁሉ አስቀድሞ ምስጋናውን አቅርቧል።
📷 kebede mekibeb
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ



Source: GetuTemesgen









No comments yet.