እስራኤል በጋዛ፣ ሊባኖስ እና ሶሪያ 1,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ገደማ መሬት መቆጣጠሯ ተገለጠ!​የፋይናንሻል ታይምስ ባደረገው…

- Advertisement -
Sidebar AD
⚡️ እስራኤል በጋዛ፣ ሊባኖስ እና ሶሪያ 1,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ገደማ መሬት መቆጣጠሯ ተገለጠ!
​የፋይናንሻል ታይምስ ባደረገው አዲስ ትንተና መሠረት፣ ከጥቅምት 7 ጥቃት በኋላ እስራኤል በጋዛ፣ በሊባኖስ እና በሶሪያ በድምሩ የሀገሪቱን የ1949 ድንበር 5% የሚያክል (1,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር) መሬት በቁጥጥሯ ሥር አውላለች።
በደቡብ ሊባኖስ፦ ከተያዘው መሬት ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው እዚህ የሚገኝ ሲሆን፣ እስራኤል ሄዝቦላህን ወደ ኋላ ለመግፋት በሚል እስከ 12 ኪሎ ሜትር ዘልቃ በመግባት “የደህንነት ቀጠና” ፈጥራለች። ሙሉ መንደሮች የወደሙ ሲሆን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ሁኔታውን “ከጋዛው ሞዴል” ጋር አነጻጽረውታል።
በጋዛ ሰርጥ፦ የእስራኤል ጦር በአሁኑ ወቅት ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የጋዛ ግዛት የተቆጣጠረ ሲሆን፣ ተጨማሪ የደህንነት ቀጠናዎችን በመፍጠሩ ምክንያት የጋዛ ህዝብ ከጦርነቱ በፊት ከነበረው ይዞታው 40% በሚሆነው ጠባብ መሬት ላይ ተጨናንቆ እንዲኖር ተገዷል።
በሶሪያ፦ እስራኤል ከኮረብታማው የሄርሞን ተራራ  በስተደቡብ ያለውን የድንበር አካባቢ ወደ 233 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚጠጋ መሬት ተቆጣጥራለች።
ኔታንያሁ ጦራቸው ከሊባኖስ “አይወጣም” ማለታቸውን ተከትሎ፣ እንዲሁም የእስራኤል ቀኝ አክራሪ ሚኒስትሮች በቦታው ላይ አዳዲስ ሰፈራዎች እንዲመሰረቱና “ሊታኒ ወንዝ” አዲሱ ድንበር እንዲሆን መጠየቃቸው፣ ይዞታው ቋሚ ሊሆን ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት በጎረቤት ሀገራት ላይ ፈጥሯል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: