በህክምና ሙከራዎች ላይ አዲስ የቁጥጥር ሥርዓት ተዘረጋ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Fastmereja I በሀገሪቱ የሚካሄዱ ማናቸውም የሕክምና ሙከራዎች (Clinical Trials) ሳይንሳዊ ተዓማኒነታቸውን የጠበቁና የዜጎችን ደህንነት ያስከበሩ እንዲሆኑ ለማስቻል አዳዲስ የቁጥጥር ጋይድላይኖችን ማዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን (ኢ.ም.መ.ባ) አስታወቀ።

የሕክምና ሙከራ አዳዲስ መድኃኒቶች፣ ክትባቶችና የሕክምና መሣሪያዎች ለግልጋሎት ከመብቃታቸው በፊት ፈቃደኛ በሆኑ ተሳታፊዎች ላይ የሚደረግ የምርምር ዓይነት ሲሆን፣ ከደረጃ አንድ እስከ አራት (Phase I – IV) ባሉ ደረጃዎች ይከናወናል።

ባለሥልጣኑ ይፋ እንዳደረገው፣ የቁጥጥር ሥራውን ሥርዓታማና ዓለም አቀፍ መሥፈርቶችን የተከተለ ለማድረግ የሕክምና ሙከራ ፈቃድ፣ የመልካም ሕክምና ሙከራ አሠራር እና የኢንስፔክሽን ጋይድላይኖችን በ2025 እትም አዘጋጅቶ ወደ ሥራ አስገብቷል።

እነዚህ መመሪያዎች ማመልከቻዎችን በጥንቃቄ ለመገምገም፣ በሙከራ ወቅት የሚከሰቱ የከፋ የጎንዮሽ ጉዳቶችን (SAE) በፍጥነት ለመከታተልና በየምርምር ተቋማቱ መደበኛ የኢንስፔክሽን ጉብኝቶችን ለማድረግ ከፍተኛ እገዛ እንደሚኖራቸዉ ተገልጿል።

ይህንን ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ የቁጥጥር አካላት፣ ስፖንሰሮች፣ ዋና ተመራማሪዎች (Pls)፣ የምርምርሥነ-ምግባር ኮሚቴዎች (IRBs) እና የጤና ሚኒስቴር በትብብር እንደሚሠሩ ተገልጿል።

በተጨማሪ በሕክምና ሙከራዎች ላይ መሳተፍ አዳዲስ ግኝቶችን ቀድሞ ለማግኘትና ለሕዝብ ጤና ዕድገት አስተዋጽኦ ለማበርከት ትልቅ ዕድል እንዳለው የተጠቆመ ሲሆን፣ ተሳታፊዎች ግን ከመሳተፋቸው በፊት ጥቅምና ጉዳቱን ተረድተው መረጃን መሠረት ያደረገ ፈቃደኝነት ማረጋገጥ እንዳለባቸው ባለሥልጣኑ አሳስቧል።





Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: