ቴምር ኮሜርሻል ኤክስፖ በሳርቤት ተከፈተ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Fastmereja I የንግድ ስፍራዎች ዋጋ መናር እና የአዋጭ ቦታዎች እጥረት ለከተማዋ ነጋዴዎች ታላቅ ፈተና በሆነበት በዚህ ወቅት፣ አልሚዎችንና ፈላጊዎችን በቀጥታ የሚያገናኝ ልዩ የገበያ ድልድይለመፍጠር ያለመው “ቴምር ኮሜርሻል ኤክስፖ” በዛሬዉ እለት በይፋ ተከፍቷል።

በሳርቤት አካባቢ፣ ከአደባባዩ ወደ ቫቲካን በሚወስደው መስመር ላይ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ ኤክስፖ፤ በዋጋ መወደድና በቦታ ምርጫ ሳቢያ የንግድ መደብር ባለቤት የመሆን ህልማቸው ለተገደበ ነጋዴዎች ታላቅ እፎይታን ይዞ መምጣቱ ተገልጿል።

ኤክስፖው ከዛሬ ግንቦት 12 እስከ ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ለአምስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ በሂደቱም በርካታ ነጋዴዎችን የሱቅ ባለቤት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የኤክስፖው አዘጋጅ እንደገለጸው፣ በኤክስፖው መድረክ ለሽያጭ በቀረቡት የንግድ ሱቆች ላይ ከ15 በመቶ በላይ የሚሆን ልዩ የዋጋ ቅናሽ መደረጉ ተገልጿል።

በተጨማሪ ደንበኞች የፋይናንስ ጫና ሳይሰማቸው የሱቅ ባለቤት መሆን እንዲችሉ የ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብርቅድመ ክፍያ ብቻ በመክፈል ውል መዋዋል የሚያስችል አሰራር የተዘረጋ ሲሆን ቀሪው ክፍያ ደግሞ ነጋዴው በስራው ሂደት እየከፈለው እንዲሄድ በሚያስችል ረጅም ጊዜ ላይበተመሰረተ አመቺ የክፍያ ሥርዓት መዋቀሩ ተመልክቷል።

የግንባታቸው ማጠናቀቂያ ላይ የደረሱ ዘመናዊ ሞሎች ለውይይትና ለሽያጭ የቀረቡት ሱቆች በወረቀት ላይ ያሉ ሳይሆኑ፣ በአሁኑ ወቅት የግንባታ አፈጻጸማቸው ከ90 በመቶ በላይ ደርሶ ወደ መጠናቀቅ የተጠጉ መሆናቸውን በመክፈቻዉ ጠቁሟል።

አልሚ ኩባንያው በአሁኑ ወቅት በከተማዋ ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ላይ ሰፊ የንግድ ማዕከላትን እየገነባ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል በፒያሳ አካባቢ አብዛኞቹ የንግድ ሱቆች የሆኑ 8 ሳይቶች፣ እንዲሁም በቡልጋሪያ እና በገላን አካባቢዎች እጅግ በርካታ ሱቆችን በውስጡ የያዘና ግንባታው በመከናወን ላይ የሚገኝ ባለ 7 ፎቅ ግዙፍ የንግድ ኮምፕሌክስ (ዘመናዊ ሾፒንግ ሞል) እንደሚገኙበት ተገልጿል።

ቴምር ፕሮፐርቲ ያዘጋጀዉ ይህ ኤክስፖ ነጋዴዎችን ከተገቢው አማራጭና ከትክክለኛው የገበያ ዋጋ ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ በመሆኑ፣ የንግድ ሱቅ ፍላጎት ያላቸው ወገኖች በሙሉ እስከ ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በሳርቤት በሚገኘው የኤክስፖ ስፍራ በአካል በመገኘት የዚህ ልዩ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2