ጣና ቂርቆስ – ከኦሪት እስከ ክርስትና

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ቀደምት ሀይማኖታዊ ቦታዎች መካከል አንዱ የጣና ቂርቆስ ገዳም ነው፡፡ ከኦሪት እስከ ክርስትና የረጅም ዓመት ታሪክ ባለቤት የሆነው ጣና ቂርቆስ ገዳም የሚገኘው በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ አስተዳደር ከጣና ሐይቅ ምስራቅ ዳርቻ ነው፡፡

ገዳሙ በክረምት ሙሉ በሙሉ በሐይቁ የሚከበብ ሲሆን፣ በበጋ ወቅት ከየብስ ጋር የሚገናኝበት ማራኪ ቀጭን ተፈጥሯዊ መንገድ አለው፡፡

የጣና ቂርቆስ ገዳም ከ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በፊት የኦሪት መስዋዕት የቀረበበት፣ ታቦተ ጽዮን ለረጅም ዓመታት ያረፈችበት፣ ቅድስት ድንግል ማርያም በስደት ለ13 ወራት የቆየችበት፣ ቅዱስ ያሬድ የዜማ እና ድጓ መጻሕፍቱን የደረሰበት፣ የኢትዮጵያን ውድ ቅርሶችን ለማከማቻ የተመረጠ እንዲሁም ከአራቱ የኢትዮጵያ መናብርት አንዱ የነበረ ድንቅ ሀይማኖታዊ መዳረሻ ነው፡፡

ከባህር ዳር ከተማ የሦስት ሰዓት የጀልባ ጉዞ ርቀት ላይ በሚገኘው ጣና ቂርቆስ ከጥንታዊው የጣና ቂርቆስ ገዳም በተጨማሪ ደምበዛ ቁስቋም፣ ቅዱስ ያሬድ እና ፅዮን ማርያም የሚባሉ ሌሎች አብያተ ክርስቲያናትም ይገኛሉ፡፡

ጥንታዊውን የኢትዮጵያ ታሪክና ቅርስ ለመረዳት፣ ለሀይማኖታዊ ጉዞ እንዲሁም ማራኪውን የጣና ሐይቅ ምስራቃዊ ዳርቻ ለመመልከት ተመራጭ የሆነውን የጣና ቂርቆስ ገዳም ትጎበኙ ዘንድ ግብዣችን ነው፡፡

Visit Amhara


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: