የቴምር ኮሜርሻል ኤክስፖ ነጋዴዎችን የሱቅ ባለቤት የሚያደርግ የሽያጭ መድረክ ከፈተ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በአዲስ አበባ ከተማ ሳር ቤት አካባቢ ለሕዝብ ክፍት ሆኖ መካሄድ የጀመረው የቴምር ኮሜርሻል ኤክስፖ፣ ነጋዴዎችና ባለሀብቶች ከ500 ሺህ ብር ጀምሮ በሚደረግ ቅድመ ክፍያ የራሳቸው የንግድ ሱቅ ባለቤት የሚሆኑበትን ልዩ ዕድል ይዞ ቀርቧል።

ከግንቦት 12 እስከ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚቆየው ይህ ኤክስፖ፣ ዘመናዊ የንግድ ማዕከላትን ለገበያ በማቅረብ ነጋዴዎችን ከቤት አከራይነት ቀንበር ለማላቀቅና የራሳቸውን የንግድ ቦታ እንዲይዙ ለማስቻል ያለመ ነው።

​ተቋሙ በኤክስፖው ወቅት ግንባታቸው ከ90 በመቶ በላይ የደረሱ አዳዲስ የንግድ ቦታዎችን ለሽያጭ ያቀረበ ሲሆን፣ ለደንበኞቹም ከ15 በመቶ በላይ የዋጋ ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል።

በፒያሳ አካባቢ ስምንት ሳይቶች፣ እንዲሁም በቡልጋሪያና በገላን በመገንባት ላይ የሚገኙ ባለ ሰባት ፎቅ ዘመናዊ የንግድ ማዕከላት ለሽያጭ የቀረቡ ሲሆን፣ በተለይም በገላን እየተገነባ ያለው ማዕከል በርካታ ሱቆችን በአንድ ላይ የያዘና ለንግድ ሥራ ምቹ ሆኖ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

​ይህ የንግድ ኤክስፖ ነጋዴዎች ቀሪውን ክፍያ በተመጣጣኝ ሁኔታና በረጅም ጊዜ እንዲከፍሉ የሚያስችል አመቺ የክፍያ ሥርዓት የዘረጋ ሲሆን፣ ይህም ዝቅተኛና መካከለኛ አቅም ያላቸው ነጋዴዎች የራሳቸው የንግድ መደብር እንዲኖራቸው ትልቅ በር የሚከፍት ነው።

የቴምር ኮሜርሻል ኤክስፖ በቀሩት ጥቂት ቀናት ውስጥ የከተማዋ ነዋሪዎችና ፍላጎት ያላቸው አካላት በሳር ቤት ከአደባባዩ ወደ ቫቲካን በሚወስደው መንገድ በሚገኘው የኤክስፖ ስፍራ በመገኘት የቀረቡትን አማራጮች እንዲመለከቱና የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪውን አቅርቧል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu #ጌጡ






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: