የነዳጅ ዋጋ መናርን ተከትሎ ዩናይትድ ኪንግደም በሩሲያ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ አላልታለችየነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን …

- Advertisement -
Sidebar AD
የነዳጅ ዋጋ መናርን ተከትሎ ዩናይትድ ኪንግደም በሩሲያ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ አላልታለች
የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተከትሎ የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት በሶስተኛ ወገን ሀገራት በተቀነባበሩ የሩሲያ የነዳጅ ምርቶች ላይ ጥሎት የነበረውን ጥብቅ ማዕቀብ አላልቷል።
ከሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው ይህ ውሳኔ፤ በአሜሪካ-እስራኤል እና ኢራን ጦርነት ምክንያት ወሳኙ የሆርሙዝ የባህር መስመር በመዘጋቱ የደረሰውን የነዳጅ አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ ያለመ ነው ተብሏል።
ከዚህም በተጨማሪ በሩሲያ የተፈጠረ የተፈጥሮ ጋዝ የባህር ትራንስፖርት ላይ የተጣሉ አንዳንድ ማዕቀቦች መላላካቸው ታውቋል።
የእንግሊዝ አውቶሞቢል ማህበር እንዳስታወቀው፤ በአሁኑ ወቅት የነዳጅ ዋጋ በሊትር 158.52 ፔንስ የደረሰ ሲሆን፤ይህም ከጦርነቱ መፈንዳት በኋላ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።
የጀት ነዳጅ ዋጋ መናርንም ተከትሎ በርካታ የአየር መንገዶች በረራዎችን ለመሰረዝና የትኬት ዋጋ ለመጨመር ተገድዋል ነዉ የተባለው።
ይህ እርምጃ እንግሊዝ በሩሲያ ላይ ጠንካራ ማዕቀብ ለመጣል ከሰባት የበለፀጉ ሀገራት ጋር በቅርቡ ያደረገችውን ስምምነት የሚጋጭ ቢሆንም፤ መንግሥት ግን አጠቃላይ ማዕቀቡ እየጠነከረ ቢሄድም አሁን ባለው ሁኔታ ተጨማሪ ተለዋዋጭ አሰራሮች አስፈላጊ መሆናቸውን ገልጿል።
አዲሱ መመሪያ ዩናይትድ ኪንግደም ከህንድ እና ከቱርክ የሚገቡ የጀት ነዳጅ ምርቶችን እንድታገኝ የሚያስችላት ሲሆን፤ ለተወሰነ ጊዜ ተፈጻሚ ሆኖ በየወቅቱ እንደሚገመገም ታውቋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
ሳራ ዮሐንስ
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: