#Ethiopia | በከባድ የልብ ሕመም ለሚሰቃዩ ሕፃናት ተስፋና ፈውስን ይዞ የመጣውና ለሦስት ቀናት የሚቆየው የነፃ የሕፃናት ልብ ቀዶ ሕክምና ዘመቻ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዛሬ በይፋ መካሄድ ጀምሯል።
ለዚህ ታላቅ ሰብአዊ ተልዕኮ ወደ ስፍራው ለገሰገሰው ዓለም አቀፍ የሕክምና ቡድን ዛሬ ጠዋት ደማቅ የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት የተደረገለት ሲሆን፣ ቡድኑም የሕይወት አድን ሥራውን ወዲያውኑ አግልግሎት መስጠት ጀምሯል።
ይህ አገር አቀፍ ጠቀሜታ ያለው ተነሳሽነት ሊሳካ የቻለው በHeart to Heart Children’s Aid፣ በኢትዮ-ኢስታንቡል አጠቃላይ ሆስፒታል፣ በፓድሬ ፒዮ ኢጣሊያ፣ በኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር እና በጎንደር ዩኒቨርሲቲ መካከል በተደረገ ጠንካራ ትብብር ሲሆን፣ ይህም በኢትዮጵያ ለሚገኙ የልብ ህመም ተጋላጭ ለሆኑ ሕፃናት ልዩ የሕክምና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የታሰበ መሆኑ ተገልጿል።
በዛሬው ዕለት ሥራቸውን በይፋ የጀመሩት ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ዓለም አቀፍ የልብ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስቶችና የሕክምና ባለሙያዎች፣ የላቀ የሕፃናት ልብ ቀዶ ሕክምናና ልዩ የልብ ሕክምና አገልግሎቶችን ለሕጻናቱ ሙሉ በሙሉ መሆኑን ጎንደር ዩኒቨርስቲ ገልጿል።
በዚህ ወሳኝ የሕክምና ዘመቻ ወደ 20 የሚጠጉ ሕፃናት ቀጥተኛ የጤና ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ዘመቻ በአሁኑ ወቅት ሕጻናቱን ያለ ምንም ክፍያ ከማከም ባለፈ፣ ወደፊት አገሪቱ በዘርፉ ራሷን እንድትችል በዓለም አቀፍ ባለሙያዎችና በአገር ውስጥ የጤና ባለሙያዎች መካከል የእውቀትና የባለሙያ ልምድ ልውውጥ ለማድረግ ይሰጣል ተብላል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሥራት አጸደወይን ዛሬ ለህክምና ቡድኑ ባደረጉት የአቀባበል መርሐ ግብር ላይ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የተቀበሉ ሲሆን፣ ለሁሉም አጋር ድርጅቶች ስላሳዩት ሰብአዊነትና ፈጣን ድጋፍ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም ይህ ተነሳሽነት የዓለም አቀፍ አጋርነት፣ የርኅራኄ እና የሕክምና አንድነት ትልቅ ማሳያ ከመሆኑም በላይ፣ ወደፊት በኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የሕፃናት ልብ ሕክምና አገልግሎትን በዘላቂነት ለመገንባትና ለማሳደግ ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረክታል ብለዋል።
በተጨማሪም ዘመቻው የሕፃናትን ሕይወት ከመታደግ ባለፈ ለቤተሰቦቻቸው ተስፋን የሚመልስና የሕፃናትን ጤናና የወደፊት ሕይወት ለመጠበቅ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸዋል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ



Source: GetuTemesgen








No comments yet.