#Ethiopia | በማህበራዊ ሚዲያ ይዘቶቹ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተሰሚነትን ያተረፈው ዲላን ፔጅ በአዲስ አበባ የተለያዩ መስህብ ስፍራዎችን በመጎብኘት ላይ ይገኛል።
ከየተለያዩ ተቋማት ምልከታውም በኋላ በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማትና የወንዝ ዳርቻ ስራዎችን ተዘዋውሮ በመመልከት ላይ ይገኛል።
ቲክቶከሩ በምልከታውም በወንዝ ዳርቻ ልማት የአረንጓዴ አሻራውን በማሳረፍ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት ስራ በማበረታት ለተከታዮቹ አጋርቷል።
ዲላን ፔጅ ጉብኝቱን አስመልክቶ በሰጠዉ አስተያየት “ይህ ጉብኝት በዓለማቀፍ ደረጃ ስለ አፍሪካ ያለውን የተዛባ አመለካከት የሚቀይር እንደሆነም ገልጿል።
በርካታ ቀናትን የሚወስደውን ታላቁን ጉዞዬን፣ በቅኝ ግዛት ባልተገዛችው ሀገር ኢትዮጵያ ጀምሬያለሁ የሚለው ተፅዕኖ ፈጣሪው ከአዲስ አበባ ባሻገርም ጥንታዊቷ የሐረር ከተማና አፋርን ጨምሮ የተለያዩ አካባቢዎችን ለመጎብኘት ማቀዱንም አስታውቋል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#AMN



Source: GetuTemesgen









No comments yet.