የደቡብ አፍሪካ መንግስት በኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰውን ጉዳት መርምሮ ውጤቱን በቅርብ ይፋ እንደሚደረግ ቃል መግባቱን የውጭ ጉ

- Advertisement -
Sidebar AD

የደቡብ አፍሪካ መንግስት በኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰውን ጉዳት መርምሮ ውጤቱን በቅርብ ይፋ እንደሚደረግ ቃል መግባቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ።

ለተፈጠረው ችግር መፍትሄ የሚያፈላልግ ልዑክ ወደ ስፍራው በቅርብ እንደሚያቀና ሚኒስቴሩ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ተናግሯል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው በሳምንቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን አካቷል፡፡

መግለጫውን የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ናቸው።

ቃል አቀባዩ በቅርቡ የተከናወኑ ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ እንቅስቃሴን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ በቅርቡ በህንድ በተካሄደው የብሪክስ አባላት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ በደቡብ አፍሪካ ጥቃት ስለደረሰባቸው ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ከአቻችው ጋር መወያየታቸውን አስረድተዋል።

በዚህም ወይይት ላይ ሁለቱ የስራ ሃላፊነት በደቡብ አፍሪካ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እየደረሱ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት መነጋገራቸው ጠቁመዋል።

በተጨማሪም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርሃኑ ጸጋዬ በኢትዮጵያ የሚገኙትን የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ኖንሴባ ሎሲ ጋር በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ አስጠርተው ማነጋገራቸውን ከቃል አቀባዩ ሰምተናል፡፡

በውይይታቸውም የሀገሪቱ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ የደረሰውን ችግር መርምሮ በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ ቃል መግባቱን አምባሳደር ነብያት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

ይህንኑ ጉዳይ የሚከታተል እና የጋራ መፍትሄ የሚያፈላልግ ልዑክም ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚላክ አክለው ጠቅሰዋል፡፡

Sheger Fm



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: