በሞጆ ከተማ የተገነባው የሴራሚክ ማምረቻ ፋብሪካ ተመረቀ
በሞጆ ከተማ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ መዋዕለ-ነዋይ የፈሰሰበት “ግራንዴር ሴራሚክ ማምረቻ ፋብሪካ” በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተመርቋል።
በ300 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈውና ግንባታው 9 ወራት ብቻ የፈጀው ይህ ፋብሪካ፣ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የሴራሚክና ፖርሲሌን ንጣፎችን ያመርታል።
በአሁኑ ወቅት የ60×60 ምርቶችን የጀመረ ሲሆን፣ በቀጣይ ሁለት ወራት የምርት መጠኖቹን እንደሚያሰፋ ታውቋል። ለፋብሪካው የሚያስፈልገው ጥሬ ዕቃ 80 በመቶው በ100 ኪሎ ሜትር ክበብ ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ጠንካራ ትስስር ፈጥሯል ተብሏል።
ይህ ተቋም የሀገር ውስጥ ፍላጎትን በመሸፈን የውጭ ምርት ጥገኝነትን ለመቀነስና የውጭ ምንዛሬን ለማዳን ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.