ልደት እና ሞት በወቅቱ በማያስመዘግቡ ነዋሪዎች ላይ 5 ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት ሊጣል ነውየአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባና…

- Advertisement -
Sidebar AD
ልደት እና ሞት በወቅቱ በማያስመዘግቡ ነዋሪዎች ላይ 5 ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት ሊጣል ነው
የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከሚቀጥለው በጀት ዓመት (ከሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም.) ጀምሮ እንደ ልደት እና ሞት ያሉ የወሳኝ ኩነት ምዝገባዎችን በወቅቱ በማያስመዘግቡ ነዋሪዎች ላይ የ5 ሺሕ ብር ቅጣት ሊጥል እንደሚችል አስታውቋል።
​የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥጋቡ ሹመይ የማኅበረሰቡን የግንዛቤ ማነስ ከግምት ውስጥ በማስገባት እስካሁን አስገዳጅ የቅጣት ውሳኔዎች ሳይተላለፉ መቆየታቸውን ገልጸው፣ አሁን ግን ደንቡን ተግባራዊ ለማድረግ መታቀዱን  ተናግረዋል።
​እንደ አቶ ጥጋቡ ማብራሪያ፤ ማንኛውም ነዋሪ፦
👉ልደትን ፦ በ90 ቀናት ውስጥ
👉ጋብቻ፣ ፍቺ፣ ሞት እና ጉድፈቻ ኩነቶችን ፦ በ30 ቀናት ውስጥ ማስመዝገብ ግዴታ አለበት።
​ነዋሪዎች የተቀመጠውን የጊዜ ቀነ-ገደብ በአግባቡ በመጠቀም ራሳቸውን ካልተፈለገ የገንዘብ ቅጣት እንዲጠብቁም ኤጀንሲው አሳስቧል።
ምንጭ: አሐዱ ራዲዮ
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1