የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ አቡሰራ እያስገነባ የሚገኘውን ታላቅ የአየር መንገድ ፕሮጀክት ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ አቡሰራ እያስገነባ የሚገኘውን ታላቅ የአየር መንገድ ፕሮጀክት ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል 40 ሚሊዮን ዶላር በማውጣት አዲስ መንደርደሪያ ለመገንባት መገደዱ ታውቋል።
በግንባታ ላይ የሚገኘው ታላቁ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እና የኢትዮጵያ አየር ኃይል በአንድ ከተማ ላይ መገኘታቸው፣ ፕሮጀክቱ ከተጠነሰሰበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ጥያቄዎችን ሲያስነሳ መቆየቱ ይታወቃል። በተለይም ግዙፍ አውሮፕላን ማረፊያ እና ተዋጊ ጄቶች የሚበሩበት ወታደራዊ ይዞታ በአንድ የአየር ክልል ውስጥ እንዴት ሊዘወሩ ይችላሉ? የሚለው ጥያቄ የብዙዎች ስጋት ነበር።
ይህንን ሊከሰት የሚችለውን ቴክኒካዊ ተግዳሮት አስቀድሞ በመለየት፣ መንግስት እና አማካሪ ድርጅቶቹ የአየር ኃይሉን ስራ ሳይገታ አዲሱን አውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት የሚያስችል የ40 ሚሊዮን ዶላር መፍትሄ በቅድመ ጥናቱ አካትተዋል። ይህ 40 ሚሊዮን ዶላር በዋነኝነት ለአዲሱ ወታደራዊ መንደርደሪያ ግንባታ፣ ለበረራ መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂዎች ዝርጋታ እና የአየር ኃይሉን ይዞታ ከአዲሱ አየር መንገድ ጋር ለማጣጣም ለሚከናወኑ የመሠረተ ልማት ማሻሻያዎች የሚውል ነው።
ይህ ሲሆን ሁለቱም ተቋማት አውሮፕላኖቻቸውን በተመሳሳይ አቅጣጫ ማስነሳትና ማሳረፍ ስለሚችሉ፣ በአውሮፕላኖች መካከል ሊፈጠር የሚችለውን የመጋጨት ስጋት ይቀንሳል። በተጨማሪም የአየር ትራፊክ ቁጥጥሩን ቀላል፣ ግልጽ እና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ያደርገዋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1