ነገ መስቀል አደባባይ በሚደረገው ፕሮግራምን ምክንያት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
በመሆኑም ፕሮግሙ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ፦
ከመገናኛ በባንቢስ ሱፐር ማርኬት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ
ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ጥላሁን አደባባይ ወይም መሾለኪያ ለከባድ ተሽከርካረዎች አጎና ሲኒማ
ከሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ለገሃር መብራት
ከንግድ ባንክ ወደ አዲስ አበባ ስቴዲዩም ቴሌ መ/ቤት
ከፒያሳ በአምባሳደር ቴአትር ወደ መስቀል አደባባይ ሀራምቤ ሆቴል
ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግስት
ከሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ለገሃር መብራት
በቦሌ መንገድ ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎፒምያ ወይም ደንበል አደባባ ጋር ከለሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
መረጃ ከተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ በተጠቀሱ አካባቢ ለአጭርም ሆነ ለእረጅም ጊዜ ተሽከርከካሪ አቆሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን ዋና መምሪያው ገልጾ መሰል ፕሮግሞች በሚዘጋጁበት ወቅት ሆነ በሌሎች የፀጥታ ስራዎች ህዝቡ እያደረገ ላለው ቀና ትብብር የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምስጋናውን እያቀረበ አሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅ እዳያጋጥማቸው አመራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡
Source: FastMereja









No comments yet.