ኒውክለስ አጠቃላይ ሆስፒታል ጥራቱን የጠበቀና ዋጋው ተመጣጣኝ የሆነ የህክምና አገልግሎት እያበረከተ መሆኑን አስታወቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የኒውክለስ አጠቃላይ ሆስፒታል በዘመናዊ የህክምና ቴክኖሎጂ የታገዘና የህብረተሰቡን አቅም ያገናዘበ የህክምና አገልግሎት በስፋት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጿል።

በሆስፒታሉ የኮሎሬክታል እና የላፓሮስኮፒ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ሱራፌል ሙላቱ እንደተናገሩት ተቋሙ የላቀ የህክምና ሙያ ክህሎትን ከርህራሄ ጋር በማጣመር ለህብረተሰቡ ተደራሽ እያደረገ ነው።

ዶክተር ሱራፌል ሆስፒታሉ የተመሰረተበት ዋነኛ ግብ አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ህክምናዎችን ለህዝቡ ማቅረብ መሆኑን ጠቁመው ለታካሚዎች የሚሰጠው አገልግሎት ጥራቱን የጠበቀና በክፍያ ረገድም መካከለኛ እንዲሆን ተቋሙ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

በሀገሪቱ እስካሁን በስፋት የማይገኙ የህክምና ዘርፎችን እና አዳዲስ ዘመናዊ መገልገያ መሳሪያዎችን በማሟላት የተሻለ የህክምና አማራጭ ለመፍጠር ሆስፒታሉ ትልቅ ራዕይ ሰንቆ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም ስፔሻሊስቱ አብራርተዋል።

ተቋሙ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ስለሚሰራበት የህክምና ዘርፍ ማብራሪያ የሰጡት ዶክተሩ ከፍተኛ የሰውነት መቅደድ ሳይደረግ በትንሽ ቀዳዳ ብቻ የሚከናወነውን የላፓሮስኮፒ ቀዶ ህክምና በተሳካ ሁኔታ እየተገበረ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ይህ ዘመናዊ አሰራር ታካሚዎች ከቀዶ ህክምና በኋላ በፍጥነት እንዲያገግሙ የሚረዳ ሲሆን እስካሁንም በርካታ ወገኖች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል። ከዚህ በተጫማሪም ሆስፒታሉ የእናቶች እና ህጻናት ህክምናን በልዩ ሁኔታ ማዕከል አድርጎ በመስጠት ላይ ይገኛል።

ኒውክለስ ሆስፒታል የዘመኑን የመመርመሪያ መሳሪያዎች እና ከፍተኛ ልምድ ያላቸውን የህክምና ባለሙያዎች በማካተት ህብረተሰቡ ያለ አላስፈላጊ ወጪ ፈጣንና አስተማማኝ የጤና መፍትሄ እንዲያገኝ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን አስረድተዋል።

#ጤና #የህክምናአገልግሎት #ሆስፒታል #ላፓሮስኮፒ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: