ብሩኖ ፈርናንዴዝን በኦልድ ትራፎርድ ለማቆየት አዲስ ውይይት ተጀምሯል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ማንቸስተር ዩናይትድ የቡድኑን መሪ እና ቁልፍ ተጫዋች ብሩኖ ፈርናንዴዝን በክለቡ ለማቆየት አዲስ የኮንትራት ስምምነት ላይ የውስጥ ውይይት መጀመሩ ተሰማ።

​ታዋቂው የስፖርት ጋዜጠኛ ፋብሪዚዮ ሮማኖ እንደዘገበው ከሆነ፣ ዩናይትድ በዚህ የክረምት የዝውውር መስኮት ፖርቹጋላዊውን አማካይ አሳልፎ የመስጠት ምንም ዓይነት ፍላጎት የለውም። ከበስተጀርባ እየተካሄደ ባለው በዚህ ንግግር ላይ የክለቡ ባለቤቶች፣ የአስተዳደር አባላት፣ የአሰልጣኝ ስታፍ እና የቡድን አጋሮቹ ተጫዋቹን በኦልድ ትራፎርድ ለማቆየት ሙሉ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

​በዚህ የውድድር ዘመን ለዩናይትድ እጅግ አስደናቂ ብቃቱን ያሳየው ፈርናንዴዝ፣ በፕሪሚየር ሊጉ ላይ 21 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማሳለፍና በአጠቃላይ 30 የጎል አስተዋፅዖዎችን በማስመዝገብ የቡድኑ የማጥቃት መስመር የጀርባ አጥንት መሆኑን በድጋሚ አስመስክሯል።

​ከአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች እና ከሳውዲ አረቢያ የሚቀርቡለትን ፈታኝ ጥያቄዎች ለመከላከል የቆረጠው ማንቸስተር ዩናይትድ፣ ከካፒቴኑ ጋር የሚያደርገውን ንግግር በሂደት ላይ ያለ ስራ (“work in progress”) በሚል በንቃት እየገፋበት ይገኛል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
​#ManchesterUnited #BrunoFernandes #FabrizioRomano #MUFC #PremierLeague #TransferNews #OldTrafford #የስፖርትዜና


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1