መድኃኔአለም በሐጢዓት ፈተና ተጠልፎ ከመውደቅ ይጠብቀን

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

እግዚአብሔር እስራኤልን ከደመና መና አውርዶ፣ ከአለት ውሀ አፍልቆ መገባቸው፡፡

እነርሱ ግን እዚህ ደጋ ላይ ቢሆንለት የውርጭ ሰደቃ እያበጀ፣ ውሀውን እያረጋ፣ መና መገብኳችሁ ይላል እንጅ ቆላ ቢሆነማ ባልተቻለውም ነበር ብለዋል። የርሱን ከሃሊነት፣ የእነርሱንም ሀሰት ሊገልጥ ቢወድ፣ ሙሴን የውሃ ምንጭ የሌለበት በረሐ ይዘሀቸው ሂድ ብሎት በዚያም መናው ወርዶላቸዋል፣ ውሀውም ፈልቆላቸዋል። ነገር ግን ነዘር የሚባል እባብ እየነከሰ ይፈጃቸው ጀመር። በዚህ ጊዜ ከሙሴ ዘንድ ሂደው ከጌታ ምህረት ቸርነት ከእኛ ኃጢአት አይታጣም በእግዚአብሔርና በአንተ ላይ ተናግረን በድለናል እባቦችን እንዲያርቅልን ወደ እግዚአብሔር አመልክትልን አሉት።

ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ቢጸልይ ከንጹህ ነሐስ የእባብ ምስል ሠርተህ ከሚገናኙበት አደባባይ ከእንጨት ላይ ስቀልላቸው አለው። እንደተባለው ቢያደርግ እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የነሐሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ። “ሙሴ እባብን በምድረ በዳ እንደሰቀለው የሰው ልጅ ክርስቶስ ይሰቀል ዘንድ አለው” ተብሎ በዮሐንስ 3÷14 እንደተነገረ፡፡ አባቶቻችንም በትርጓሜ ወንጌል የበረሐው እባብ የዲያብሎስ፤ የብረቱ እባብ የጌታ ምሳሌ ነው። በእባብ መርዝ እንዳለበት በዲያብሎስም ፍዳ ኃጢአት አለበት።

በነሐሱ እባብ መርዝ እንደሌለበት በጌታም ፍዳ ኃጢአት የለበትም። የነሐሱ እባብ በእባብ አምሳል መሰቀሉ ጌታ እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ለመሰቀሉ ምሳሌ ነው። ክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል በተሰቀለ ጊዜ፤ የተሰቀለው የክብር ባለቤት ሰማይን የፈጠረ ነውና ፀሐይ ጨልማለች፣ ጨረቃ ደም ሆኗል፣ ከዋክብት ረግፈዋል።

ገዳማውያኑም በመስቀል የተደረገልንን ማዳን እያሰቡ ዓለምን ንቀው፣ ስጋቸውን ጎድተው ይከተሉታል፡፡ የጽድቃቸው አክሊል እርሱ መድኃኔ ዓለም የሚወደኝ መስቀሌን ተሸክሞ ይከተለኝ እንዳለ፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1