የዘንድሮው ሀገራዊ ምርጫ የሀገረ-መንግሥት ሥርዓታችን መሠረት ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የዘንድሮው ሀገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ሀገረ-መንግሥታዊ ሥርዓት የሚጠነክርበትና የዴሞክራሲ ልምምድ አንድ ደረጃ ከፍ የሚልበት ወሳኝ አጋጣሚ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ (ዐረፋ) በዓል ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ላይ ነው።

የዐረፋ በዓል ማኅበረሰባዊ በዓል መሆኑን፣ ሰዎች በግላቸው ሳይሆን ከቤተሰብ፣ ጎረቤትና ማኅበረሰብ ጋር በመተሳሰብና በመተጋገዝ የሚያከብሩት መሆኑን ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህ ማኅበራዊ ትስስር ለዜጎችና ለሀገር ደኅንነት ወሳኝ መሆኑን አስምረውበታል።

ከዚሁ ማኅበራዊ ኃላፊነት ጋር በማያያዝም ምርጫን ዋነኛው የማኅበራዊና ዜግነታዊ ግዴታ መወጫ መሣሪያ አድርገው አቅርበውታል።

“ያለ ሕዝብ ተሳትፎ ዴሞክራሲ አይሳካም። ያለ ምርጫም የሕዝብ ተሳትፎ ምሉዕ አይሆንም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ መጪው ምርጫ ብዝሃ-ድምፅ የሚሰማበትና የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የሚመሰረትበት ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ መሆኑን አብራርተዋል።

በመሆኑም መላው ሕዝበ ሙስሊም በዓሉን ሲያከብር ማኅበራዊ ግዴታውን በመወጣት ብቻ ሳይወሰን፣ በመጪው ምርጫ በድምፅ መስጫ ካርዱ ዴሞክራሲያዊ መብቱን ለማረጋገጥ ዝግጅት እንዲያደርግ ሀገራዊ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
#PMAbiyAhmed #Democracy #EthiopianElection #CivicDuty #EthiopianBroadcastingCorporation


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: