#FastMereja I ግብፅ በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ የፖለቲካና የደህንነት ስምምነቶች ላይ የባህሩ ተጋሪ ያልሆኑ የውጭ ሀገራት ጣልቃ መግባታቸውን ፈጽሞ እንደማትቀበል በይፋ አስታወቀች።
እሁድ ዕለት በካይሮ በተካሄደው ዘጠነኛው የግብፅ-የመን ስትራቴጂካዊ ውይይት ላይ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ ከየመኑ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሻያ አል-ዚንዳኒ ጋር ባደረጉት ምክክር ነው የሀገራቸውን ጽኑ ቋሚ አቋም ግልጽ ያደረጉት።
ይህ የግብፅ ውሳኔ በቀይ ባህር ቀጣና ላይ እያደገ የመጣውን የዓለም አቀፍ ኃይሎች ፍላጎትና የተፈጠረውን የጂኦፖለቲካዊ ውጥረት ተከትሎ የመጣ ሲሆን፣ የደህንነት ጥበቃው በራሳቸው በባህሩ ተጋሪ በሆኑ የቀጣናው ሀገራት ብቻ ሊመራ እንደሚገባ የሚያሳይ ነው። ውይይቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከርና በቀጣናው ሰላም ዙሪያ በጋራ ለመስራት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
Source: FastMereja









No comments yet.