አሜሪካ በሆርሙዝ የባህር በር ለንግድ መርከቦች ጥበቃ መስጠት ጀመረች
የአሜሪካ ባህር ኃይል “የነፃነት ፕሮጀክት በሚል የተሰየመውን ስራውን በድጋሚ በማንቀሳቀስ፣ በሆርሙዝ የባህር በር ለሚያልፉ የንግድ መርከቦች ወታደራዊ ጥበቃ ማድረግ መጀመሩን The Wall Street Journal ዘግቧል።
ባለፈው መጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ በባህረ ሰላጤው ውስጥ ተጣብቃ የቆየችው እና 2 ሚሊዮን በርሜል ድፍድፍ ዘይት የጫነችው የግሪክ ግዙፍ የነዳጅ ጫኝ መርከብ በአሜሪካ ባህር ኃይል ጥበቃ ተደርጎላት ከኦማን የባህር ዳርቻ እንድትወጣ የተደረገ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ወደ ህንድ እያመራች ትገኛለች።
የባህር ኃይል ባለስልጣናት እንደገለጹት፣ በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ግዙፍ የነዳጅ ጫኝ እና የኮንቴይነር መርከቦችን ጨምሮ ወደ 12 የሚጠጉ መርከቦችን በዚሁ የባህር መስመር በሰላም ለማሳለፍ እቅድ ተይዟል።
@Seledadotio

No comments yet.