በኪነ-ጥበብ አፍቃሪያን ዘንድ ስሙ በጉልህ የሚነሳው ሰዐሊ መሐሪ ተሾመ፣ አዳዲስ የስዕል ስብስቦቹን (ስራዎቹን ) ለህዝብ ዕይታ ያበቃበትን ልዩ የጥበብ ዐውደ ርዕይ በማዘጋጀት ስራዎቹን ለህዝብ በማሳየት ላይ ይገኛል።
ስነ-ጥበብ ለሀገርና ለህብረተሰብ ያለው ፋይዳ በቀላል የሚገለጽ አይደለም። እያንዳንዱ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ—የምንጠቀምባቸው ቁሳቁሶች ዲዛይን፣ የስነ-ህንጻ ጥበብ፣ አልባሳት፣ የምንኖረበት የአካባቢ ገጽታ አልፎ ተርፎም የምንጠቀማቸው የገንዘብ ኖቶች ሳይቀሩ—በቀጥታ ከዲዛይን ጥበብ ጋር የተቆራኙ ናቸው። ዲዛይን ደግሞ የስዕል አንድ አካል ነው ።ጥበብ በሰዎች ህይወት ውስጥ ሰፊ ተፅዕኖ ፈጣሪና የሀገር መገለጫም መሆኑ ይታወቃል።
ይህ እግዚቢሽን እየቀረበበት የሚገኘው “በአርታዊ ጋለሪ” (Artawi Gallery)
ከተቋቋመ ሶስት ዓመታት በላይ አስቆጥሯል። ጋለሪው በነዚህ ዓመታት ውስጥ በርካታ የስነ-ጥበብና የፎቶግራፊ ጥቦችን ስራዎችን ለዕይታ በማቅረብ፣ ሰዓሊያንና ፎቶግራፈሮችን ከህብረተሰቡ ጋር በማገናኘት እንዲሁም አዳዲስ የውይይት መድረኮችን በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
“ስውር መልክ” (The Hidden Form) በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የዚህ ልዩ የጥበብ እግዚቢሽን የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ግንቦት 15 ቀን የተከናወነ ሲሆን፣ እግዚቢሽኑ እስከ ሰኔ 7 ቀን ድረስ ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል።
ቦታ 👉 ቦሌ ብራስ ኬኬር ሆቴል ህንጻ 2ኛ ፎቅ ላይ
የጥበብ ወዳጀች ና የስዕል አፎቃሪዎች ሁሉ በቦታው በመገኘት የሰዐሊውን ሀሳብ በቅርፅና በቀለም የሚናገሩ ድንቅ ስራዎች እንዲታደሙና የስነ-ጥበቡ ተሳታፊ አካል እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።



Source: FastMereja









No comments yet.