አሜሪካ  በሆርሙዝ የባህር በር ለንግድ መርከቦች ጥበቃ መስጠት ጀመረች​የአሜሪካ ባህር ኃይል “የነፃነት ፕሮጀክት በሚል የተሰየ…

- Advertisement -
Sidebar AD
አሜሪካ  በሆርሙዝ የባህር በር ለንግድ መርከቦች ጥበቃ መስጠት ጀመረች
​የአሜሪካ ባህር ኃይል “የነፃነት ፕሮጀክት በሚል የተሰየመውን ስራውን በድጋሚ በማንቀሳቀስ፣ በሆርሙዝ የባህር በር  ለሚያልፉ የንግድ መርከቦች ወታደራዊ ጥበቃ ማድረግ መጀመሩን The Wall Street Journal ዘግቧል።
​ባለፈው መጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ በባህረ ሰላጤው ውስጥ ተጣብቃ የቆየችው እና 2 ሚሊዮን በርሜል ድፍድፍ ዘይት የጫነችው የግሪክ ግዙፍ የነዳጅ ጫኝ መርከብ  በአሜሪካ ባህር ኃይል ጥበቃ ተደርጎላት ከኦማን የባህር ዳርቻ እንድትወጣ የተደረገ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ወደ ህንድ እያመራች ትገኛለች።
​የባህር ኃይል ባለስልጣናት እንደገለጹት፣ በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ግዙፍ የነዳጅ ጫኝ እና የኮንቴይነር መርከቦችን ጨምሮ ወደ 12 የሚጠጉ መርከቦችን በዚሁ የባህር መስመር በሰላም ለማሳለፍ እቅድ ተይዟል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: