የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለኢድ አል-አድሃ በዓል የበዓሉን አከባበር መመሪያዎች አስተላለፈ።
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እና የኢድ አከባበር አስተባባሪ አቢይ ኮሚቴ፣ ነገ ረቡዕ ለሚከበረው 1447ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል የጸጥታ፣ የሎጂስቲክስ እና የሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶችን የተመለከቱ መመሪያዎችን ዛሬ በሰጡት መግለጫ ይፋ አድርገዋል።
በዓሉ በአዲስ አበባ ስታዲየም እና በዙሪያው የሚከበር ሲሆን፣ መጨናነቅን ለመቀነስ ምእመናን በክፍለ ከተሞች በአወሊያ፣ በኢማም አህመድ መስጂድ፣
በገርመንት አደባባይ፣ በኡመር ኢብኑል ኸጣብ መስጂድ፣ ከከነማ ፋርማሲ (ከተባበሩት) እስከ ፔፕሲ አደባባይ ያሉ ስፍራዎች ላይ መሰገድ እንደሚችሉ ገልጸዋል።
የኢድ ሰላት በጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ላይ የሚጀመር በመሆኑ ምእመናን ቀደም ብለው እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል።
ምክር ቤቱ፣ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ምእመናን ከጸጥታ አካላት ጋር እንዲተባበሩ አጥብቆ ጠይቋል።
@Seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.