የመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር ዘመናዊ የግንባታ ግብዓቶችን አስገባ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር ባለፈው ዓመት በጋዜጠኛ ሰይፉ ፋንታሁን አስተባባሪነት በተሰበሰበው የሕዝብ ድጋፍ፣ ለረጅም ጊዜ የሚያገለግሉ ጥራት ያላቸው የፊኒሺንግ እቃዎች እና ዘመናዊ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ላይ ይገኛል።

ማህበሩ እስካሁን ድረስ በአጠቃላይ 109 ኮንቴይነሮችን የተረከበ ሲሆን፣ እነዚህ ግብዓቶች በማህበሩ እየተከናወኑ ለሚገኙ ሰፊ የግንባታ ፕሮጀክቶች እንደ ዋና ድጋፍ የሚውሉ ናቸው።

​በተረከቡት የፊኒሺንግ እቃዎች ውስጥ 54 ኮንቴይነር ፖርስሊን፣ 7 ኮንቴይነር ግራናይት፣ 20 ኮንቴይነር የተለያዩ የፊኒሺንግ ማቴሪያሎች እና 6 ኮንቴይነር የባኞ ቤት እቃዎች ይገኙበታል።

ከዚህ በተጨማሪም 400 ሚሊዮን ብር በሆነ ወጪ 22 ኮንቴይነሮች የሆኑ ዘመናዊ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች መግባታቸው ታውቋል።

ከእነዚህ ማሽነሪዎች መካከል የኮንክሪት መለኪያ ጣቢያ፣ ታወር ክሬን፣ የኮንክሪት መስመር ፓምፕ፣ የኮንስትራክሽን ሊፍቶች፣ የኮንክሪት ቡም ፓምፕ፣ አምስት የኮንክሪት ትራክ ሚክሰሮች፣ ሁለት የኤሌክትሪክ ጀነሬተሮች፣ ኤክስካቫተር፣ ዊን ሎደር እና መሰል ማሽኖች እንዲሁም ለሁሉም ማሽነሪዎች የሚሆኑ መለዋወጫ እቃዎች ይገኙበታል።

​ከዚህ በተጨማሪም ሙሉ ክፍያ የተፈጸመባቸው ከ50 በላይ ኮንቴይነሮች በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንደሚገቡ የተገለጸ ሲሆን፣ በእነዚህ ኮንቴይነሮች ውስጥ ሀንድሪል፣ እስቲል ለስ፣ ሰባት ግዙፍ ሊፍቶች፣ የተለያዩ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ሶኬቶች፣ የእሳት አደጋ መከላከያ ፓምፖች እና ማጥፊያዎች፣ መስታወት፣ የአሉሚኒየም ፓነል እንዲሁም የተለያዩ የውኃ ቧንቧዎች ይካተታሉ።

​ማህበሩ ያስገባቸው እነዚህ ዘመናዊ ማሽነሪዎች እና የግንባታ ግብዓቶች፣ በቅርቡ ግንባታው ለሚጀመረው በ7,000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ለሚያርፈው ባለ 27 ወለል ሁለት ሕንፃዎች እንዲሁም በ56 ቅርንጫፎች ላይ ለተጀመሩ የግንባታ ፕሮጀክቶች መጠናቀቅ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።

እነዚህን ፕሮጀክቶች በብቃት ለመገንባት የሚያግዙት እነዚህ ግብዓቶች፣ የማህበሩን አቅም በማጎልበት ተደራሽነቱን ለማስፋት ታቅዶ እየተከናወነ ያለ ሂደት ነው።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu #ጌጡ






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2