“ዶናልድ ትራምፕ” የተባለው ጎሽ በመንግሥት አስቸኳይ ጣልቃ ገብነት ከእርድ ተረፈ!በባንግላዲሽ ለዒድ አል-አድሃ የዓረፋ በዓል …

- Advertisement -
Sidebar AD
“ዶናልድ ትራምፕ” የተባለው ጎሽ በመንግሥት አስቸኳይ ጣልቃ ገብነት ከእርድ ተረፈ!
በባንግላዲሽ ለዒድ አል-አድሃ የዓረፋ በዓል መስዋዕት ሊሆን ጥቂት ሰዓታት ብቻ ቀርተውት የነበረውና በልዩ መልኩ ወርቃማ ፀጉር ያለው “ዶናልድ ትራምፕ” የተባለው ብርቅዬ ነጭ ጎሽ በመንግሥት አስቸኳይ ጣልቃ ገብነት ሕይወቱ ተርፏል!
ይህ 700 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ግዙፍ ጎሽ በጭንቅላቱ ላይ ያለው ወርቃማና ውብ ፀጉር የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን የፀጉር ስታይል ስለሚመስል ነበር “ትራምፕ” ተብሎ የተሰየመው።
የጎሹ ቪዲዮዎች በሶሻል ሚዲያ ላይ በቫይራል መሰራጨታቸውን ተከትሎ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰዎች ከሩቅ ቦታዎች ጭምር እየመጡ ከእሱ ጋር ፎቶ ለመነሳት እርሻው ላይ ታይቶ የማይታወቅ መጨናነቅ ፈጥረው ነበር።
ጎሹ ለበዓሉ እርድ ቀድሞ ተሽጦ የነበረ ቢሆንም በሕዝቡ ከፍተኛ ፍላጎትና በቦታው ላይ በተፈጠረው የደህንነት ስጋት ምክንያት የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስቸኳይ ጣልቃ ገብነት አድርገዋል። ለገዢውም ሙሉ ገንዘቡ ተመላሽ ተደርጎ ጎሹን ከእርድ ታድገውታል።
አሁን “ትራምፕ” ሙሉ በሙሉ ደህንነቱ ተጠብቆ በዳካ ወደሚገኘው ብሔራዊ መካነ አራዊት ተወስዷል።
እዚያም ልዩ እንክብካቤ እየተደረገለት ለዕይታ የሚበቃ ሲሆን ይህ ብርቅዬ እንስሳ ዕድሜው ገና ወጣት በመሆኑ ለቀጣይ ዓመታት በሰላም በጥበቃ ስር እንዲኖር ተወስኗል።
Via Fox News
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: