ቀደምት ኢትዮጵያውያን ‘አስከሬን የማቃጠል’ ልማድ ነበራቸው?

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በኢትዮጵያ አፋር ክልል የተገኘ አዲስ አርኪኦሎጂያዊ ግኝት፣ የሰው ልጅን የስልጣኔና የባህል ታሪክ ወደኋላ ሊመልስ የሚችል አዲስ ፍንጭ ይዞ ብቅ ብሏል።

በመካከለኛው አዋሽ፣ ‘ፋሮ ዳባ’ በተባለ የምርምር ቦታ ላይ የተደረገ ጥናት የሰው ልጅ አስከሬንን የማቃጠል (Cremation) ልማድ ከምናስበው በላይ እጅግ ጥንታዊ ሊሆን እንደሚችል አመላክቷል።

​የፊንላንዱ ዑውሉ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎችን ዋቢ በማድረግ ስፑትኒክ የዜና ምንጭ እንደዘገበው፣ በስፍራው ወደ 100 ሺህ ዓመታት ገደማ ያስቆጠሩ የእንስሳት ቅሪተ አካላት፣ የድንጋይ መሣሪያዎች እና ቢያንስ የሦስት የሆሞ ሳፒያንስ (የዘመናዊ ሰው) ከፊል አጽሞች ተገኝተዋል።

​የዚህ ግኝት ዋነኛ መነጋገሪያ ነጥብ የሰው አጥንቶቹ ዝም ብለው የነደዱ ሳይሆን፣ ሆን ተብሎ ለከፍተኛ ሙቀት የተጋለጡ መሆናቸውን የሚያሳዩ ሳይንሳዊ ምልክቶች መገኘታቸው ነው። ተመራማሪዎቹ በመንጋጋ ጥርስና በአቅራቢያው ባሉ የአጥንት ስብርባሪዎች ላይ የሚከተሉትን ለውጦች አስተውለዋል፦

አጥንቶቹ በቀጥታ ከከፍተኛ እሳት ጋር መገናኘታቸውን ያሳያል።

በዘመናዊ የፎረንሲክ ሳይንስ ትንተና መሠረት፣ አጥንቶቹ በሕይወት በሌሉበት ወቅት ሆን ተብሎ የመቃጠል ሂደት እንደደረሰባቸው ያረጋግጣል።

​እስካሁን ባለው የታሪክ እውቀት፣ አስከሬንን የማቃጠል ልማድ ከዚህ ፍጹም ዘግየት ብሎ የተጀመረ እንደሆነ ነበር የሚታመነው። ነገር ግን ይህ የአፋር ግኝት በታሪክ ተመራማሪዎች ዘንድ ሙሉ በሙሉ ከተረጋገጠ፡

​”የአስከሬን ማቃጠል ልማድን ታሪክ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ዓመታት ወደኋላ የሚመልሰው ይሆናል። ይህም ሆሞ ሳፒያኖች ገና ከአፍሪካ ሳይወጡና በመላው ዓለም ሳይሰራጩ በፊት፣ እጅግ የረቀቀ የማኅበራዊና የባህል ሥነ-ሥርዓት (Ritual) እንደነበራቸው ትልቅ ማረጋገጫ ይሆናል ተብሏል።”

​ኢትዮጵያ አሁንም የሰው ልጅ መገኛነቷን ብቻ ሳይሆን፣ የቀደምት ስልጣኔዎችና የማኅበራዊ እሴቶች መፈጠሪያ ምድር መሆኗን ይህ አዲስ ምርምር በድጋሚ እያሳየ ይገኛል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
​#ኢትዮጵያ #የሰውልጅመገኛ #አርኪኦሎጂ #አፋር #ሆሞሳፒያንስ #ታሪክ #ሳይንስ #የአስከሬንማቃጠል #የአዋሽሸለቆ #አዲስግኝት #channel1tv


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1