#Ethiopia | በኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ስልጠናን በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ።
ኦቪድ አካዳሚ ከፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት፣ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ከኦቪድ ኮንስትራክሽን እንዲሁም ከጣሊያኑ ስኪልአፕ እና ከስፔኑ ኢንስቲቱዮቶ ኢኪጋይ ጋር በመተባበር ዴልታ ዲጂታል ኢምፓወሪንግ ለርኒንግ ቱልስ ፎር አፍሪካ የተሰኘውን ፕሮጀክት በይፋ ማስጀመሩን በዛሬው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
የዚህ ፕሮጀክት ዋነኛ ግብ የወጣቶችን የክህሎት አቅም ማሳደግና በዘመናዊ የዲጂታል ስልጠናዎች ማብቃት ነው።
በዚህም በዘርፉ የሚታዩ የክህሎት ክፍተቶችን በመሙላት፣ የሀገሪቱን ተመጣጣኝ የመኖሪያ ቤቶች አቅርቦት ጥረት ለመደገፍ ታቅዷል።
ከቴክኒክ ስልጠናው ባሻገር ወጣቶች የራሳቸውን የስራ እድል መፍጠር እንዲችሉ የዲጂታል እና የአመራር ክህሎት ድጋፍ ይደረግላቸዋል።
በተጨማሪም በአውሮፓ እና በኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ስርዓቶች መካከል የቴክኖሎጂ ሽግግር ለመፍጠርና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ የሚያስችል አሰራር ይዘረጋል።
ይህ በትምህርት ተቋማት፣ በኢንዱስትሪዎች፣ በስልጠና ማዕከላት እና በልማት አጋሮች ትብብር የሚተገበረው ፕሮጀክት፣ በአቅም ግንባታ፣ በምርምርና ፈጠራ፣ በስራ ፈጠራ ልማት እንዲሁም ማህበራዊና ኢንዱስትሪያዊ ችግሮችን በሚፈቱ ተግባራዊ አቀራረቦች ላይ ትኩረት ያደርጋል።
በተለይም በኮንስትራክሽን ዘርፍ ያለውን የክህሎት ክፍተት በመሙላት ረገድ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል።
መርሃ ግብሩ በሙከራ ደረጃ ከቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች እና እድሜያቸው ከ18 እስከ 29 ዓመት በሆኑ ወጣቶች ጋር የሚጀመር ሲሆን፣ በቀጣይም በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና አግኝቶ ወደ ሁሉም ተቋማት ለማስፋፋት መታቀዱ ተገልጿል።
#የቴክኒክናሙያ #ዲጂታልቴክኖሎጂ #የስራፈጠራ #የወጣቶችክህሎት #ኮንስትራክሽን #ትምህርት #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen









No comments yet.