በምርጫ ጣቢያ ክልል ምን አይነት ተግባራት እንደተከለከሉ ያውቃሉ?

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ግንቦት 24 ቀን የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ በሚሰጥበት ቀን ከምርጫ አስፈፃሚዎች፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና የግል እጩ ወኪሎች፣ ከቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት እና ከተፈቀደላቸው የምርጫ ታዛቢዎች በስተቀር መራጮች ያልሆኑና ድምፅ የሰጡ ሰዎች በምርጫ ጣቢያው ክልል ውስጥ መገኘት የለባቸውም፡፡

በኢትዮጵያ ምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ላይ እንሰፈረው ፤ ማንኛውም ሰው ከምርጫ ጣቢያ 500 ሜትር ዙሪያ መለስ ርቀት ውስጥ በስካር መንፈስ ውስጥ ሆኖ፣ የጦር መሳሪያ ይዞ ወይም በሌላ በማናቸውም ፀጥታን በሚያደፈርስ ሁኔታ ውስጥ መገኘት የለበትም፡፡

በዚህ ሁኔታ ከተገኘም የምርጫ ጣቢያ ኃላፊው የጸጥታ ኃይሎችን ድጋፍ በመጠየቅ አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ ሊያደርግ ይችላል::

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
#EthiopianBroadcastingCorporation #Election2026 #Ethiopia


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1