በኢትዮጵያ በቴሌግራም የሚደረግ የክሪፕቶ ግብይት (P2P Trading) ሊቆም ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በቴሌግራም ላይ የክሪፕቶ ግብይት መድረክ የሆነው ዋሌት (Wallet )፣ ከግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ብር የሚደረጉ የክሪፕቶ ግብይቶችን (P2P Trading) እንደሚያቆም አስታወቀ።

ይህ ውሳኔ የተወሰደው ከሀገሪቱ የፋይናንስ ህጉን መሰረት አድርጎ እንደሆነ ነው የገለጸው።

ከተጠቀሰው ቀን በኋላ ሁሉም በኢትዮጵያ ብር የሚደረጉ የP2P ማስታወቂያዎች በሙሉ ይጠፋሉ ሲባል፤ አዲስ ማስታወቂያዎችንም መለጠፍም አይቻልም።

ከቀነ ገደቡ በፊት የተጀመሩ ግብይቶች በተለመደው አሰራር መሠረት መፈጸም ይቻላል ተብሏል።

ከዚህ ቀደም ባይናንስ በተመሳሳይ መልኩ በኢትዮጵያ ብር የሚደረጉ የክሪፕቶ ግብይቶችን (P2P Trading) ከግንቦት 7 ጀምሮ ማቆሙ ይታወሳል።

ብሔራዊ ባንክ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ሥርዓት ያለው የዲጂታል ፋይናንስ ተሳትፎ እንዲኖር የሚያስችል አጠቃላይ የቁጥጥር ማዕቀፍ ለማዘጋጀት ከዓለም አቀፍ አቻ ተቆጣጣሪዎችና ከአገር ውስጥ ባለድርሻ አካላት ጋር በንቃት እየመከረ መሆኑን ሲገለጽ ቆይቷል ሲል ቲክቫህ ዘግቧል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: