የአሽከርካሪዎች ስልጠና አልቀረም” አሽከርካሪዎች ራሳቸው ለስልጠና በመረጡበት የአሽከርካሪ ተቋም ከፍለው ስልጠናውን የሚከታተሉ …

- Advertisement -
Sidebar AD
የአሽከርካሪዎች ስልጠና አልቀረም‼️
” አሽከርካሪዎች ራሳቸው ለስልጠና በመረጡበት የአሽከርካሪ ተቋም ከፍለው ስልጠናውን የሚከታተሉ ይሆናል “- የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

➡️ ” የመጀመሪያውን ምዕራፍ የምዘና ሂደትም በቀጣይ 15 ቀናት ውስጥ ይጀመራል “

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ ያሉ አሽከርካሪዎች በሙሉ በድጋሚ እንዲሰለጥኑና እንዲመዘኑ በማድረግ፣ በብቃት ማነስ ምክንያት የሚከሰቱ አደጋዎችን ለመቀነስ ያለመ ሀገራዊ ፕሮጀክት መንደፉን አሳውቋል።
ለዚህም ይረዳ ዘንድ አጠቃላይ የሰነድ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ተግባር መገባቱን አመልክቷል።
” አዲሱ የምዘና ሂደት ከተለመደው አሰራር በተለየ መልኩ ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ነው። ከምዝገባ ጀምሮ እስከ ስልጠና እና ሰርተፊኬሽን ድረስ ያለው ሂደት ከሰው ንክኪና ጣልቃ ገብነት የጸዳ እንዲሆን ተደርጎ ተቀርጿል ነው ” ያለው።
” ይህ የምዘና ሂደቱን ግልጽ በማድረግ ብቃቱ ያለው አሽከርካሪ ብቻ መንገድ ላይ እንዲገኝ ያስችላል ”  ብሏል።
ይህንን ሀገራዊ ፕሮጀክት በይፋ ለማስጀመር ደግሞ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከኤስ ዲ ኤስ ሴፍቲ ኤንድ ድራይቪንግ ስኪልስ (SDS) ከተባለ ድርጅት ጋር የሥራ ውል ስምምነት ተፈራርሟል።
ስምምነቱን የሚኒስትር ዴኤታው አቶ በርኦ ሀሰን እና የድርጅቱ አመራሮች በጋራ ፈርመዋል።
ፕሮጀክቱ በቅድሚያ ማንኛውንም የንግድ ተሽከርካሪ በሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች ላይ የሚጀመር ሲሆን፤ ማንኛውም አሽከርካሪ አዲሱን የብቃት ምዘና አልፎ ብቃቱን በተጨባጭ በማረጋገጥ ብቻ እንዲያሽከረክር የሚያስገድድ ጥብቅ የቁጥጥር ሥርዓት ይዘረጋል ተብሏል።
በመሆኑም የሚመለከታቸው አሽከርካሪዎች ለሚጀመረው ምዝገባና ስልጠና አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
ከእዚህ ጋር በተያያዘ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ማብራሪያ ከትራንስፖርት ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የጠየቀ ሲሆን ሚኒስቴሩ አተገባበሩ በምዕራፍ የተከፋፈለ እንደሚሆን ገልጿል።
የመጀመሪያው ምዕራፍ የተመዛኞች ምዝገባ እና ስልጠና በቀጣይ 15 ቀናት ለመጀመር እቅድ መያዙን ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቀድሞውኑ መንጀ ፍቃድ ሲወጣ ተከፍሎና ስልጠና ተወስዶ በመሆኑ አሁን ይተገበራል የተባለው ስልጠናና ምዘና ክፍያ ይኖረው እንደሆነ ጠይቋል።
ሚኒስቴሩ ፦
– ለምዝገባ
– ለምዘና
– ለሰርተፊኬት የሚከፈል ምንም አይነት ክፍያ የለም ብሏል።
ነገር ግን ” አሽከርካሪዎች ራሳቸው ለስልጠና በመረጡበት የአሽከርካሪ ተቋም ከፍለው ስልጠናውን የሚከታተሉ ይሆናል ” ሲል ገልጿል።
የስልጠና ጊዜ ቆይታውም 5 ቀናት መሆኑን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አሳውቋል።#ቲክቫህ
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2