ጅማ ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ ገዝነት ለመሸጋገር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታወቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ራስ ገዝ ለመሆን የዝግጅት ሥራዎችን አጠናቆ የሚኒስትሮች ምክር ቤትን የራስገዝነት አዋጅ እየተጠባበቀ እንደሚገኝ የጅማ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው የራስገዝነት አዋጅ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት ሦስት ዓመታት የሌሎች ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎችን ተሞክሮ በመውሰድ የተለያዩ ሥራዎችን ሲሠራ መቆየቱን የጠቀሱት ዩኒቨርሲቲው የሪፎርም ጉዳዮች ዋና አማካሪ ተክሉ ታፈሰ (ዶ/ር)፤ በዚህም የራስገዝነት ፖሊሲዎችን በማዘጋጀት፣ ተቋማዊ የሪፎርም መመሪያዎችን በማርቀቅ እንዲሁም በተዘጋጁ ሰነዶች ላይ ከቦርድና ከባለድርሻ አካላት ጋር የመገምገም እና ሰነዶችን ለትምህርት ሚኒስቴር የመላክ ሥራ ሲሠራ መቆየቱን አስረድተዋል።

ዩኒቨርሲቲው በገንዘብ ራሱን ለመቻል ከመንግሥት በጀት በተጨማሪ፤ የተለያዩ የፋይናንስ አማራጮችን ማስቀመጡን አማካሪው ተናግረዋል ሲል ፕረስ ድርጅት ዘግቧል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
#digitalhagerie #JU #university


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1