ሙሉ የተሽከርካሪ እገዳ ተጣለበጋምቤላ ክልል ከነገ ጧት ጀምሮ በክልሉ የሚገኙ ማንኛውም ተሽከርካሪ እንቅስቃሴ የማይፈቀድና የተከ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ሙሉ የተሽከርካሪ እገዳ ተጣለ‼️
በጋምቤላ ክልል ከነገ ጧት ጀምሮ በክልሉ የሚገኙ ማንኛውም ተሽከርካሪ እንቅስቃሴ የማይፈቀድና የተከለከለ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቀ።
ከነገ ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ/ም ከጧት ጀምሮ እስከ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ የተለየ የይለፍ ፊቃድ ካልተሰጠው በስተቀር ማንኛውም የመንግሥት፣ የንግድ እና የግል ተሽከርካሪዎች፣ ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች/ባጃጅ እና ሞተር ሳይክል በሙሉ እንቅስቃሴ እንዲያቆሙ የተወሰነ ሲሆን ይህንን መመሪያ ተግባራዊ በማያደርጉ አሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ የሆነ ሕጋዊ እርምጃ የሚወሰድባቸው መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር አቶ ዶሮ ካሩ አሳስበዋል።
ከነገ ግንቦት 23 ቀን 2018 እስከc ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ/ም
በልዩነት የተፈቀደላቸው  ለድንገተኛ ሥራ (Emergency) ብቻ የሚንቀሳቀሱ የመብራት ኃይል፣ የቴሌኮሙኒኬሽን እና አምቡላንሶች ሲሆን የይለፍ ወረቀት መያዝና ሲጠየቅ የማሳየት ኃላፊነትና ግዴታ  እንዳለባቸውም ተገልጿል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: