በደሴ ከተማ የውሻ እብደት በሽታ አሳሳቢ የማህበረሰብ ችግር እየሆነ መምጣቱ ተገለፀ ባለፋት ዘጠኝ ወራት ውስጥ የውሻ ንክሻ ላጋ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በደሴ ከተማ የውሻ እብደት በሽታ አሳሳቢ የማህበረሰብ ችግር እየሆነ መምጣቱ ተገለፀ
ባለፋት ዘጠኝ ወራት ውስጥ የውሻ ንክሻ ላጋጠማቸው ከ3መቶ በላይ ለሆኑ ሰዎች ህክምና መስጠቱን የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታውቋል፡፡
የሆስፒታሉ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሙያ አቶ ብርሃኑ አዱኛ ከብስራት ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት አሁን ላይ የውሻ እብደት በሽታ አሳሳቢ የማኅበረሰብ ችግር እየሆነ ይገኛል።
ባለፋት ዘጠኝ ወራት በሆስፒታሉ ለ3 መቶ 3 የእብድ ውሻ ንክሻ ተጠርጣሪዎች እና ለ172 የኬሚካል መመረዝ ላጋጠማቸው ሰዎች ህክምና መሰጠቱን አስረድተዋል።
በደሴ ከተማ 34.3 በመቶ፣ በደቡብ ወሎ 29.4 በመቶ እንዲሁም በሰሜን ወሎ 21.5 በመቶ የሆነ ከፍተኛ የእብድ ውሻ ንክሻ ስርጭት ተመዝግቧል።
ግኝቱ በአካባቢው በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች የእብድ ውሻ ንክሻ በሽታ ስርጭት መስፋፋቱን የሚያሳይ መሆኑን አቶ ብርሀኑ ጠቅሰው ይህም በክልሉ እየጨመረ ያለውን የህብረተሰብ ጤና ስጋት አጉልቶ እንደሚሳይ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል ።Via_dagu
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1