ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት የአፍሪካ ምርጥ ብራንድ በመሆን ተሸለመ
#Ethiopia | የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ በአህጉራዊ መድረክ ያስመዘገበውን አንጸባራቂ ድል በድጋሚ አድሷል። ጣቢያው በተከታታይ ለሁለት ዓመታት የአፍሪካ ምርጥ ብራንድ በመሆን የመመረጥ ታላቅ ክብርን አግኝቷል።
ይህ በኢንተርናሽናል ደረጃ የተሰጠው እውቅና የጣቢያውን ተመራጭነት እና ጥራት ያስመሰከረ ሲሆን፣ ተወዳጁ የእሁድን በኢቢኤስ የፕሮግራም ክፍልም ለዚህ ስኬት የበኩሉን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
የጣቢያው አመራሮችና ሰራተኞች ይህንን ታላቅ ድል ለሁለተኛ ጊዜ በመቀዳጀታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፣ ለቀጣይ ስራዎቻቸውም ትልቅ መነሳሳትን እንደሚፈጥርላቸው አስታውቀዋል።
#ebs #ebstv #africanbrands #media #ethiopianmedia #television #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen









No comments yet.