ፔዤ ዳግም ሻምፒዮን

- Advertisement -
Sidebar AD

መድፉ በክብር ተሸንፏል ! OHO BIG GABI …
እግር ኳስ ከቡዳፔስት በስሜት ሀዘንና ደስታ ቅፅበታዊ ልውውጦች መሃል ! Champions League Classic .

በኤፍሬም የማነ

#Ethiopia | በእነዛ ሽርፍራፊ ሰከንዶች የፔናሊቲ ድራማ ራያ ኤዜን አዳነ ። ራያ አርሰናል አዳነ ። መድፉ ሞቶ ተነሳ ። የፔናሊቲው ድራማ ከቡዳፔስት ቀጠለ ። ከሜንዴዝ መሳት በኋላ ፔዤ ብልጫውን ወሰደ ። የመድፉ ለ120 ደቂቃ የዘለቀ የጀግንነት ተጋድሎ በBig Gabi አምስተኛዋ ወሳኝ ፔናሊቲ ላይ ተወሰነ ። መድፈኞቹ ተጨነቁ ። ዓለም በስሜት ከፍ ዝቅ አለ ። የመድፉ የድል አባት አርሴን ቬንገር ከማጋሊሽ ወሳኝ ፔናሊቲ ጋር በጭንቅ ታጥፈው ታዩ ። ንጉስ ኦነሪ በCBS ስቱዱዮ አርሰናል ከተባለ እናት ሀገሩ ጋር በስሜት ተንቆራጠጠ ። ማጋሊሽ በቀጥታ ፔናሊቲ ተመቶበት ካላዳነው የፔዤው በረኛ ሳፋኖቭ ተፈጠጠ ። ፀንቶ ለአርሰናል ድል ሲዋደቅ የዋለው ብራዚላዊ የመድፉ ግድግዳ ወሳኝ ፔናሊቲ በዛች አጋጣሚ ከቡዳፔስት ሰማይ ስር በረረች ። ፔዤ ሻምፒዮን ሆነ ። አርሰናል በጀግንነት ተዋድቆ ተሸነፈ ። እግር ኳስ ከቡዳፔስት በስሜት ሀዘንና ደስታ ቅፅበታዊ ልውውጦች ተሞላች ። የፀናው የመድፉ የድል ምኞት ትጋት በመጨረሻ ከብቃት ባሻገር እንደ ሎተሪም በሆነው ፔናሊቲ ታጠፈ ። አርሰናል ሁለት ወደ ፎሪና ሰማይ በለቀቃቸው ፔናሊቲዎች አማካኝነት የህይወት ዘመን ወደር አልባው የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ህልሙን ሳያሳካ ቀረ ። መድፉ በክብር ተሸነፈ ። መድፉ በክብር ተዋድቆ ተረታ ። ከፑሽካሽ አሬና እግር ኳስ በሁለቱ ኋያላን ፍጥጫ ለ120 ደቂቃ ዘልቆ ለፔናሊቲ በተዳረገ የህይወት ገፅ ተመሠለ ። ስሜት ከፍ አለ ። ተስፋ ነገሰ ። መውጣት መውረድ መውደቅ መነሳት ፀፀት ደስታ ቁጭት እንባ ከቡዳፔስት ተፈራረቁ ። ማግኘት ማጣት መሳት ማዳን በሚሊዮኖች ላይ በእነዛ የፔናሊቲ ቅፅበቶች ተፈራረቁ ። በመጨረሻም 120 ደቂቃዎች ተሻግሮ ለፔናሊቲ የደረሰው ድራማ ፓሬዚያኑን ዳግም አነገሰ ። አርሰናል በክብር እጅ የሰጠው አሳዛኙ ተሸናፊ ሆነ ። እግር ኳስ ኳስ ይዞ መሽከርከር ብቻ እንዳልሆነ መድፉ በፀና ተደናቂ የመከላከል ቅርፁ አረጋገጠ ።

በላቀ የጨዋታ ዝግጅነት የዳበረው በታክቲክ የታጠረው ትንቅንቅ የዘመናዊው እግር ኳስ ሁለት የእግር ኳስ ቀለሞችን አሳየ ። እግር ኳስ በመድፉ የመከላከል ከፍታ ውስጥ የፔዤ የማጥቃት አቅምን አፈዘዘ ። ፓሬዚያኑ ከመድፉ ካቴና ፊት ተቆልፈው ዋሉ ። ድራማ ከቡዳፔስት ክዋክብቶቹ ከሜዳው ለድል ተዋደቁ ። ከመድፉ ግድግዳ ፊት እንደወትሮው እንደልቡ መንፈላሰስ ለፓሬዚያኑ ብርቅም ሆነ ። የመድፉ ባስ ከፓሬዚያኑ ፊት ፀንቶ ቆመ ። አርቴታ ከመጀመሪያ ቋሚ አሰላለፉ አንስቶ የመረጠው የጨዋታ ስትራቴጂው በአግባቡ ሲያዋጣው ታየ ። የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን አውራ ጆዜን መሰለ ። አርሰናል የጣሊያንን አዙሪ ካቴናን አስናቀ ። ፔዤ እንደወትሮው መንቀሳቀስ ተሳነው ። ፓሬዚያኑ የአቻ ጎል ለማግኘት ያውም በፔናሊቲ 65 ደቂቃ ታተሩ ። የመድፉ የደረጀ የመከላከል ቅርፅ የፔዤ የማጥቃት ጥራትን ለአፋልጉኝ ማስታወቂያ አበቃ ። የመድፉ ካቴና ጀገነ ። የመጫወቺያ ቦታ የተነፈጉት የፔዤ ኮኮቦች እንደ ወትሮው ማንፀባረቅ ተሳናቸው ። ዘንድሮ ብቻ በቻምፒዮንስ ሊጉ 44 ጎል አዝንቦ ለቡዳፔስት ፍፃሜ የደረሰው ፔዤ ከመድፉ ግድግዳ ፊት ህይወት ከበደው ። ተጋጣሚዎቹ ላይ እንደ ልቡ በጎሎቹ የሚዘንጠው ፔዤ የአቻዋን ጎል በዴምቤሌ ፔናሊቲ አገኘ ። ፔዤ 75 በመቶ ኳስ ተቆጣጥሮ በዘለቀው ጨዋታ የመድፉ የዳበረ አጥርን መጣስም ተሳነው ። ለጨዋታው ቀልብ ገዢ ፉክክር የሚያዋጣውን የጨዋታ ቅኝት በቡድኑ ዓመቱን ሙሉ በነበረ ጥንካሬ ላይ ተመርኩዞ ተግባራዊ ያደረገው አርቴታ የፓሬዚያኑ የተለመደ ህበረ ትርዒትን አከሰመ ። ፔዤ 21 ወደ ጎል ሞክሮ 4 ብቻ ታርጌታቸውን የጠበቁ ሆኑ ። የመድፉ የፀና የLow Block ኮንክሪትን ጥሶ ማለፍ ለእነ ክቫራ ዴምቤሌ ዱዌ ብርቅ ሆነ ። ተቀይሮ የገባው ብራኮላ የተሻለ ራያን ቀረበ ። ያለ ኳስ ቁጥጥር ተጋጣሚው አርሰናል በጨዋታ መሃል ያለውን ጥንካሬ ከጨዋታው በፊትም የመሰከረው ሉዊስ ኤኔሪኬ ምርጡ ስብስቡ ከመድፉ ኮንክሪት ፊት ከመቼውም ግዜ በላይ የማጥቃት ሀሳቦች ተፋልሰው ታዩ ።

የተፈራው ክቫራ በማስኬራ ተቆለፈ ። ዱዌ ዴምቤሌ ፈዘዙ ። የፔዤ ፍሬ አልባ የኳስ ቁጥጥር ፉርሽ ሆነ ። መከላከል ጀገነ ። አርሰናል ፔዤን አሰረ ። ከሰሜን ለንደን ቡዳፔስት የደረሰው የመድፉ አውቶብስም በjose park the Bus ስታይል ሉዊስ ኤኔሪኬን አቁነጠነጠ ። የመድፉ እንደ አለት የጠነከሩ የፀኑ አጥሮች የሆኑት ማጋሊሽና ሳሊባ በራይስ እና ስኬሊ ሽፋን ለፓሬዚያኑ ፈተና ሆነ ። ጉዳት ያጋጠመው ሄንካፔ ቅያሪ ቀድሞ በጨረሰው አርቴታ እስከመጨረሻው በጀግንነት ተሰዋ ። እንደ ጨዋታ ዕቅዱ ጥሩ አጀማመሩ የመጨረሻዎቹ የጨዋታ ሂደቶች ላይ ጠንቃቃው አርቴታ በቁልፍ የጨዋታው ቅያሪ ውሳኔዎቹ ተፈተነ ። አርቴታ ከ120 ደቂቃ በኋላ ተጋድሎ በኋላ ከመጨረሻው የፔናሊቲ መቺ ምርጫ ውሳኔዎቹ የመዱፉ የክብር ሽንፈት አይረሴው ቁጭት ሆኑ ። ከፔናሊቲው ድራማ በፊት በተጨማሪው 30 ደቂቃ ዴክላን ራይስን ጨርቅ ያስጣለች ማይክ አርቴታን ያሳበደች የሜንዴዝ ማዱኬ ፋወል ከVAR የዳኛው ዕይታ መታለፍ ጋር ሌላው አነጋጋሪም ነበር ። ይህ የመድፉ አርሰናል ወርቃማው የውድድር ዓመት መልክ ነው ። ይህ የፓሬዚያኑ እንደ ልብ ከኳስ ጋር የሚፈነጩ ክዋክብቶችን ከጎሉ ፊት ቆልፎ የዋለው የመድፉ ካቴና ታላቁ ተጋድሎ ነው ። ይህ አርሰናል ወደ ፎሪ እና ወደ ሰማይ በላካቸው ሁለት ፔናሊቲዎች ፀፀት ታጅቦ በጀግንነት እስከ መጨረሻው ተዋድቆ እጅ የሰጠበት የመድፉ የህይወት ከፍታ ጉዞ አሳዛኙ ሌላኛው የቻምፒየንስ ሊግ ምሽት የክብር ገፁ ነው ። ፔዤ ሻምፒዮን ። ናስር አልከሊፋ የፔዤው ቢሊየነር አባት ሉዊስ ኤኔሪኬ ቀምሞ ባወቀረው ቡድናቸው እንደፎከሩት ሁለተኛውን የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ በተከታታይ ድል ነስተዋል ። የፈረንሳይ ሊግም ምስጋና ለፓሬዚያኑ እያለ በድጋሜ በትልቁ የክዋክብቶች መድረክ የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ላይ ዳግም ነግሷል ።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: