ለአረህማን እንግዶች ያለክፍያ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ምርመራ ተከናወነ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በመካ የሚገኘው የሁጃጆች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ከአብሳር የዓይን ሕክምና ማዕከል ጋር በመተባበር ለ400 የሀጅ ተጓዦች ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ምርመራ እንዲያገኙ አድርጓል።

በምክትል ፕሬዝደንት ማዕረግ የሀጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ዶክተር ሙሐመድ ሷሊህ እንደገለጹት፣ እንግዶች ጤንነታቸው ተጠብቆ የሀጅ ስርዓታቸውን በሰላም መፈጸም እንዲችሉ የተለያዩ ነጻ አገልግሎቶች ሲቀርቡላቸው ቆይቷል።

ኃላፊው ለአብሳር የዓይን ሕክምና ማዕከልና ለዚህ በጎ ተግባር መሳካት ጥረት ላደረጉ የጽህፈት ቤቱ ባልደረቦች እንዲሁም ሌሎች ተባባሪ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ የህክምና አማካሪ ዶክተር አብዱሰመድ መሀመድ በበኩላቸው፣ ምርመራ ከተደረገላቸው ተጓዦች መካከል 100 የሚሆኑት በቀጣዩ ቀን በጂዳ ሆስፒታል ነፃ የሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና እንደሚያገኙ አብራርተዋል።

በተጨማሪም ነጻ የምርመራ አገልግሎት ያገኙት እነዚህ የዓረህማን እንግዶች እንደየአስፈላጊነቱ ልዩ ልዩ የሕክምና ድጋፎች ተደርገውላቸዋል።

#ሀጅ #መካ #የአይንህክምና #ጤና #ኢትዮጵያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1