የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎችን ፍጹም ፍትሃዊ እና ከስህተት የጸዱ ለማድረግ፣ ሙሉ በሙሉ በባትሪ ኃይል የሚሰራ ዘመናዊ የቴ

- Advertisement -
Sidebar AD

የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎችን ፍጹም ፍትሃዊ እና ከስህተት የጸዱ ለማድረግ፣ ሙሉ በሙሉ በባትሪ ኃይል የሚሰራ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ኳስ ጥቅም ላይ ሊውል መሆኑ ተመልክቷል።

ዘንድሮ ውድድሩን በጋራ የሚያስተናግዱት አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ከመላው ዓለም የሚመጡ ስፖርተኛችንና የእግር ኳስ አፍቃሪያንን ለመቀበል የመጨረሻ ዝግጅታቸውን እያጠናቀቁ ይገኛሉ።

ይህ የዓለም ዋንጫ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሶስት ሀገራት በአንድ ጊዜ የሚስተናገድ ከመሆኑም በላይ በስፖርቱ ዓለም አዲስ የቴክኖሎጂ ምዕራፍ የሚከፍትበት ሆኗል።

ከ1970 ጀምሮ ለዓለም ዋንጫ ኳሶችን እያመረተ የሚገኘው አዲዳስ ኩባንያ፣ ዳኞችን በከፍተኛ ሁኔታ ለመርዳት የሚያስችል “ኮኔክቲድ ቦል ቴክኖሎጂ” (Connected Ball Technology) የተገጠመለትንና ትሪዮንዳ የተሰኘውን አዲስ የኤሌክትሮኒክስ ኳስ ይፋ አድርጓል።

የአዲዳስ ቃል አቀባይ እንደገለጹትብበኳሱ ውስጥ የተገጠመው መመርመሪያ (Sensor) ያለ ባትሪ ኃይል መስራት ስለማይችል ኳሱ ከእያንዳንዱ ጨዋታ በፊት የግድ ቻርጅ መደረግ ይኖርበታል።

ኳሱ ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ ሙሉ ጨዋታውንና ከዚያ በላይ በብቃት ማገልገል እንዲችል በጨዋታው ዕለት በስታዲየሙ ውስጥ በተዘጋጀ ልዩ የኃይል መሙያ መደርደሪያ (Cradle) ላይ ቻርጅ ይደረጋል።

ለዚህም በኢንደክሽን አማካኝነት በገመድ አልባ ሥርዓት ቻርጅ የሚደረግ ከፍተኛ ጥራት ያለው ባትሪ ጥቅም ላይ ውሏል።

ይህ ባትሪ ሙሉ በሙሉ ለመሙላት 90 ደቂቃ አካባቢ የሚፈጅ ሲሆንንበጨዋታ ላይ እያለ እስከ 6 ሰዓታት የማገልገል አቅም አለው።

ይህም የአንድን ከፍተኛ የደረጃ ጨዋታ ክፍለ-ጊዜ እጥፍ መቆየት የሚችል ያደርገዋል። በተጨማሪም ኳሱ ከሜዳ ውጭ በሚሆንበት ጊዜ ራሱን ወደ እረፍት ሁነታ (Hibernation mode) በመቀየር ባትሪው ሳይባክን ለቀናት እንዲቆይ ያደርጋል።

በኳሱ ውስጥ በልዩ የመደገፊያ ስርዓት (Suspension system) ተይዞ የተገጠመ 500Hz inertial measurement unit (IMU) የተሰኘ የቪዲዮ ረዳት ዳኝነት (VAR) መረጃዎችን የሚልክ ስስ የኮምፒውተር ቺፕ ይገኛል።

ይህ ሴንሰር እያንዳንዱን የኳስ ንክኪ በከፍተኛ ፍጥነት የሚከታተል ሲሆን የሚከተሉትን ውሳኔዎች በሜዳ ላይ በሴኮንዶች ውስጥ ለመወሰን ይረዳል፦

* ከጨዋታ ውጪ (Off-side) የሆኑ አቋቋሞችን በትክክል መለየት፣
* ኳስ በእጅ መነካቱን (Handballs) ማረጋገጥ፣
* እና ሌሎች አወዛጋቢ ሁነቶችን በቪዲዮ ረዳት ዳኝነቱ (VAR) አማካኝነት በፍጥነት መፍታት።
አዲዳስ እና የቴክኖሎጂ አጋሩ ኪኔክሶን (Kinexon) እንዳስታወቁት፣ ይህ ቴክኖሎጂ ቀደም ሲል በሁለት የፊፋ ውድድሮች እንዲሁም በዩሮ 2024 እና 2025 ላይ የተሞከረ ሲሆን፣ በጨዋታ መሃል ባትሪ አልቆበት የተቀየረ አንድም ኳስ አጋጥሞ አያውቅም።

ባለፈው የ2022ቱ የኳታር ዓለም ዋንጫ ላይም ተመሳሳይ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ውሎ የነበረ ቢሆንም፣ የዘንድሮው የ2026ቱ ኳስ ግን የሴንሰር አቀማመጥ ለውጥ ተደርጎበታል። በቀደመው ኳስ ሴንሰሩ የተቀመጠው በኳሱ መሃል ላይ ሲሆን፣ በዘንድሮው ስሪት ግን ሴንሰሩ የተገጠመው በኳሱ የጎንዮሽ አካል (Side) ላይ ተቀብሮ ነው።
ኳሱ ከቴክኖሎጂው ባሻገር፣ ሶስቱን አስተናጋጅ ሀገራት ለማክበርና ለመወከል ሲባል በደማቅ ቀይ፣ አረንጓዴ እና ሰማያዊ ቀለማት የተሸለመ ሲሆን፤ የካናዳው የሜፕል ቅጠል (Maple leaf)፣ የሜክሲኮው ንስር (Eagle) እና የአሜሪካው ኮከብ (Star) ምልክቶች በሥነ-ጥበባዊ መልኩ ተካተውበታል።




Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1