ኢዜማን ምረጥ ያለው ኢህአዴግ በእስራት ተቀጣ…በደቡብ አሪ ወረዳ፣ ገድር ቀበሌ በምርጫ ዕለት የተከለከለ የፖለቲካ ቅስቀሳ በ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ኢዜማን ምረጥ ያለው ኢህአዴግ በእስራት ተቀጣ…
በደቡብ አሪ ወረዳ፣ ገድር ቀበሌ በምርጫ ዕለት የተከለከለ የፖለቲካ ቅስቀሳ በማድረጉ የተከሰሰው አቶ ኢህአዴግ ኃይሉ የ6 ወር ቀላል እስራት ተፈረደበት።
​የዐቃቤ ህግ ክስ እንደሚያስረዳው፣ ተከሳሹ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ምርጫ ጣቢያ አቅራቢያ ድምፅ ለመስጠት ወደ ጣቢያው ይሄድ የነበረን ወጣት ለኢዜማ ድምፅ እንዲሰጥ በመገፋፋት በምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 የተደነገገውን ክልከላ ጥሷል።
​ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የደቡብ አሪ ወረዳ ፍርድ ቤት፣ የዐቃቤ ህግን የሰው ምስክሮች እና የተከሳሹን የእምነት ክህደት ቃል ካዳመጠ በኋላ ተከሳሹ መከላከያ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ ጥፋተኛ ብሎታል። ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ የሦስት ልጆች አሳዳጊ መሆኑን እንደ ማቅለያ በመቀበል፣ በቀጣይ ለሌሎችም ማስጠንቀቂያ ይሆን ዘንድ በ6 ወር ቀላል እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አሳልፏል። ፍርዱ ለሁለት ዓመት በግልጽ ገደብ እንዲፈጸም ታዟል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: