ይቺም ሻማ ሰልችታለች

- Advertisement -
Sidebar AD

‼️

#Ethiopia | በአገራችን ለሚቀጥሉት ብዙ አሥርት ዓመታት ምናልባትም አሁን በሕይወት የምንገኝ ሰዎች በአጠቃላይ ሳናይ የምንሞተው ነገር የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ”ኃላፊነቴን በአግባቡ ስላልተወጣሁ ሥራዬን በፈቃዴ ለቅቄያለሁ፤ ከ’ኔ የተሻለ ሰው ይምራው” የሚለው ነው።

በአርሲ ዞን በኦርቶዶክስ ክርስትና አማኞችና አብያተ-ክርስትያናት ላይ በተደጋጋሚ ጥቃቶች እየተሰነዘሩ ብዙ ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ሞተ፤ አብያተ-ክርስትያናትና ቅርሶችም ወደሙ፤ በነዋሪዎቹ ዘንድ ሥጋትና ጥርጣሬ ሰፈነ።

ይሄን ተደጋጋሚ ጥቃት ለማስቀረት የተሠራ ሥራ አለ? ሰላም ማስከበር 100% የክልሉ መንግሥት ሥራ አይደለም እንዴ? ምን አድርጓል? ሰላም ማስከበር ካቃታቸው በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት ”አልቻልንም፤ የፌዴራል መንግሥት ጣልቃ ይግባልን” ይባላል እኮ! መቼም ”እኔ ለዚህ ኃላፊነት ብቁ ሆኜ አልተገኘሁም፤ የተሻለ ብስለትና ልምድ ያለው ሰው ይተካኝ” የሚሉ ኃላፊዎችን በሕይወት እያለን እንደማናይ ዕሙን ነው።

ሰው ባለቀ ቁጥር ይቺን ሻማ ብልጭ ማድረግ ምን ፋይዳ አለው? ይሰለቻል። የክልሉ መንግሥት ለዚህ ዞን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሕዝቡን ይጠብቅ። በጊዜ መፍትሔ ካልተሰጠው የዚህ ዳፋ የማይተርፈው ሰው የለም።

እንደ አንድ ተርታ ዜጋ በደረሰው ጉዳት ሐዘኔን ለመግለጽ እወዳለሁ።

ሐውለት አሕመድ-


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1