በአሜሪካ የሚገነባው የኢቦላ ማዕከል በኬንያ ከፍተኛ ተቃውሞና የፍርድ ቤት እገዳ ገጠመው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በኬንያ ላይኪፒያ አየር ማረፊያ አቅራቢያ በአሜሪካ መንግሥት ሊገነባ የታቀደው የኢቦላ ለይቶ ማቆያ ማዕከል በኬንያውያን ዘንድ ብርቱ ተቃውሞ እያስነሳ ነው።

​ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ማዕከሉ ለኬንያ ጠቃሚ የሆነ የጤና ትብብር አካል ነው ቢሉም፣ በናንዩኪ ከተማ የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ተቃውሞ ግን ወደ ግጭት አምርቶ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተረጋግጧል።

​ማዕከሉ በጎረቤት አገራት በኢቦላ የተጠቁ አሜሪካውያንን ወደ አገራቸው ከመመለሳቸው በፊት ለማቆያነት ታስቦ የተዘጋጀ ቢሆንም፣ የኬንያ ሐኪሞች ማህበርና ዜጎች በሕዝብ ጤና ላይ ከፍተኛ ስጋት እንደሚፈጥር በመግለጽ እየተቃወሙት ይገኛሉ።

​ይህንን ተከትሎ የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የውጭ መንግሥታት በአገሪቱ የኢቦላ ማዕከል እንዳያቋቁሙ በማዘዝ በግንባታው ላይ ጊዜያዊ እገዳ የጣለ ሲሆን፣ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ግን ከኬንያ መንግሥት ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት እያደረጉ መሆኑ ታውቋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
​#ኬንያ #አሜሪካ #የኢቦላማዕከል #ዊሊያምሩቶ #የጤናስጋት #ናንዩኪ #የፍርድቤትእገዳ


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: