በአርሲ ሀገረ ስብከት በደረሰ ጥቃት የ13 ሰዎች ሕይወት አለፈ የአንድ ክፍለ ዘመን ዕድሜ ያለው ቤተ ክርስቲያንም ወደመ

- Advertisement -
Sidebar AD

የአርሲ ሀገረ ስብከት ሚዲያን ጠቅሶ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ጥቃቱ የተፈጸመው ከግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአሰኮ፣ በሺርካ እና በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳዎች ላይ ነው። በጥቃቱ ሳቢያ የ101 ዓመት ዕድሜ ያለው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት የፈረሰ ሲሆን፣ በካራ ኩፍተና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ላይ ደግሞ ከፍተኛ ዘረፋ ተፈጽሟል። በዚህም ምክንያት ምእመናን የቤተ ክርስቲያኑን ጽላት ይዘው ለመሰደድ ተገድደዋል።

ብፁዕነታቸው እንደገለጹት፣ በጥቃቱ ሳቢያ በአሰኮ ወረዳ ብቻ ከ280 በላይ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን፣ የነዋሪዎች መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል፤ ከብቶቻቸውና ንብረቶቻቸውም ተዘርፈዋል።

“ኦርቶዶክሳውያኑ ተወልደው ካደጉበት፣ ወልደው ከሳሙበት ቀያቸው በማንነታቸውና በሃይማኖታቸው ብቻ እየተለዩ ጥቃት ደርሶባቸዋል” ያሉት ሊቀ ጳጳሱ፣ ከጥቃቱ የተረፉት ነዋሪዎች ይዘውት የሸሹት እምነታቸውን ብቻ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት ሜዳ ላይ ወድቀው ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን ጠቁመዋል።

በተፈጸመው በዚህ ጥቃት ሕይወታቸውን ያጡት 13ቱ ሰዎች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፦
1. አቶ ደምረው አበራ (የ70 ዓመት)
2. አቶ ከፈለኝ ልክየለው (የ56 ዓመት)
3. አቶ ሐይሉ ንጉሴ (የ70 ዓመት)
4. አቶ እሸቴ ዳመና (የ42 ዓመት)
5. አቶ አበባየሁ ዳኜ (የ42 ዓመት)
6. አቶ ሰሙ አባይነህ (የ70 ዓመት)
7. ስማቸው ያልተጠቀሰ 1 የአካባቢው ሚሊሻ
8. አቶ አማረ በላይነህ (የ80 ዓመት)
9. ተሬ ደሴ (የ25 ዓመት)
10. ወጣት ገነነ ጥላሁን (በሺርካ ወረዳ)
11. ሙርቴሳ ጥላሁን (በሺርካ ወረዳ)
12. አቶ ንጉሱ ማንደፍሮ (በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ)
13. አቶ በቀለ ኃ/ሚካኤል (በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ)

ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ በተፈጸመው አረመኔያዊ ድርጊት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን በመግለጽ፣ “የሞቱትን ወገኖቻችንን እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸውን በመንግሥተ ሰማያት ያሳርፍልን፤ ያዘኑትን እና በሜዳ ላይ ወድቀው የሚገኙትን የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን እግዚአብሔር ያጽናናልን” ሲሉ የጸሎትና የማጽናኛ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: