በጋና “ባሕሩን እከፍላለሁ” በማለት የሙሴን ታሪክ ለመድገም የሞከረው ግለሰብ ለትዝብት ተዳረገ​ራሱን “ነቢይ” አድርጎ የሚጠራው…

- Advertisement -
Sidebar AD
በጋና “ባሕሩን እከፍላለሁ” በማለት የሙሴን ታሪክ ለመድገም የሞከረው ግለሰብ ለትዝብት ተዳረገ
​ራሱን “ነቢይ” አድርጎ የሚጠራውና በተደጋጋሚ ስለ ዓለም ፍጻሜ ትንቢት በመናገር የሚታወቀው ኤቦ ኖህ (እውነተኛ ስሙ ኢቫንስ ኢሹን) የተባለ ጋናዊ፣ በባሕር ማዕበል ተመትቶ ሲወሰድ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል (ቪዲዮ) በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ ሆኗል።
​ሰሞኑን በጋና የባሕር ዳርቻ ላይ የተከናወነው ይህ ክስተት፣ ግለሰቡ የነቢዩ ሙሴን ታሪክ በመምሰል ሁለቱን እጆቹን ወደ ባሕሩ ዘርግቶ “ባሕሩን ለመክፈል” ሲሞክር ያሳያል።
ሆኖም ግን፣ ሳይታሰብ የመጣ ከባድ ማዕበል ክፉኛ ከመታው በኋላ በውሃው ፍሰት ተገፍቶ ሲወሰድና ሊወድቅ ሲል በምስሉ ላይ ታይቷል።
​ይህ የተቀረጸ ምስል በቲክቶክ እና ኤክስ ላይ በስፋት የተሰራጨ ሲሆን፣ በርካታ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ድርጊቱን በትዝብት እየተመለከቱት ይገኛሉ።
​ኖህ ከዚህ ቀደም “እ.ኤ.አ. ታኅሣሥ 25 ቀን 2025 ዓለም ትጠፋለች” የሚል ትንቢት ተናግሮ የነበረ ሲሆን፣ የጋና ባለሥልጣናትም የሕዝብ ሽብር በመፍጠር ወንጀል ከዚህ ቀደም በቁጥጥር ስር አውለውት እንደነበር ተገልጿል።
@Seledadotio
@Seledadotio


Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: