“የጽምዶ ጥምረት” በርካታ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ቡድኖችን እያካተተ መሆኑ ተገለጠ​በኤርትራ እና ህወሃት መካከል የተጀመረውና “ጽ…

- Advertisement -
Sidebar AD
“የጽምዶ ጥምረት” በርካታ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ቡድኖችን እያካተተ መሆኑ ተገለጠ
​በኤርትራ እና ህወሃት መካከል የተጀመረውና “ጽምዶ” (Ximdo) በመባል የሚታወቀው አዲሱ የፖለቲካ ትስስር፣ አሁን ላይ በርካታ የኢትዮጵያ የታጠቁና የፖለቲካ ተቃዋሚ ቡድኖችን ወደማካተት እየሰፋ መሄዱን አፍሪካ ኢንተለጀንስ  ዘግቧል።
📌 የአዲስ አበባውን ማዕከላዊ መንግስት የሚቃወሙት የህወሃት/ትግራይ መከላከያ ኃይል አመራሮች፣ በቅርቡ በሱዳን የወደብ ከተማ ፖርት ሱዳን ከተደረጉ የኤርትራ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ከሱዳን ጦር ኃይል ተወካዮች ጋር ስብሰባ ማድረጋቸው ተረጋግጧል።
​ይህ በኤርትራ መንግስት  አስተባባሪነት እየተመራ ያለው ጥምረት የህወሃትን “የአሮጌው ጎራ ጨምሮ፣ እንደ ፋኖ  ያሉ፣ የኦብነግ የተገነጠሉ ክንፎችን እና ሌሎች ታዋቂ የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን በአንድ ጥላ ስር ለማሰባሰብ እየሰራ እንደሆነ የደህንነት ምንጮች ጠቁመዋል።
​የሰሜኑ ጦርነት ወቅት ኤርትራ እና ህወሃት እርስ በእርስ የገጠሙ ደመኛ ጠላቶች የነበሩ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን “የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው” በሚለው መርህ የአዲስ አበባውን መንግስት ለመጫንና የራሳቸውን የፖለቲካ ህልውና ለማስጠበቅ ስልታዊ ህብረት ፈጥረዋል።ይህ አዲስ የሀይሎች መሸጋሸግ በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ እና በሱዳን መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ እያሻከረው ሲሆን፣ ቀጠናዊ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1