… ግፍን፣ ጭካኔንና ጭፍጨፋን አንለምድም!

- Advertisement -
Sidebar AD

* ሙሼ ሰሙ እንደጻፉት!…

#Ethiopia | ማንነትና ሐይማኖትን ሰበብ አድርጎ ሰዎችን መጨፍጨፍ የሚከለክለውን የተባበሩት መንግስታት የጂኖሳይድ ኮንቬንሽን ኢትዮጵያ እአአ ጁላይ 11 ቀን 1949 ዓ.ም መፈረም ብቻ ሳይሆን ስምምነቱን Ratify በማድረግ ማንነትና ሐይማኖት ሰበብ ያደረገ ጭፍጨፋ የሕግ ተጠያቂነትን እንዲያስከትል የተስማማች የመጀመርያዋ ሀገር ናት።

ይህ የሆነው ከ77 አመት በፊት በአባቶቻችንና በአያቶቻችን ዘመን ነው። ዛሬ ከ77 ዓመት በኋላ ግን የሕጉ ፋይዳ፣ የሰው ልጅ ክቡርነት ውሉ ጠፍቶን ፊት ለፊት አዛኝ መሳይ ቅቤ አንጓች በዝግ በር ጂኖሳይድን የሚያሞግሱና የሚያቆለጳጵሱ ዜጎችን እንደ አሸን ያፈራች አሳፋሪና ዘግናኝ ሀገር መገለጫ ሆነናል።

የጸጥታ ተቋማት ዜጎችን ከጂኖሳይደሮች መከላከል፣ ሕግ ማስከበር፣ ማክበርና ሰላምን ማረጋገጥ የተሳናቸው መሆኑ ሳያንስ የመንግስት ሚዲያዎች የሚመለከታቸው የሰብአዊ መብት ተቋማት የተጨፈጨፉ ንጽሃን ዜጎችን ሞት ለመዘረከርና ለመዘገበ የሚጸየፉና የሚተናነቃቸው ሆነዋል።

ኢትዮጵያ አለም አቀፍ ስምምነቱ ግዴታ የሚጥልባቸው በተለይ ሐይማኖትና ማንነትን መሰረት አድርገው ጂኖሳይድ የሚፈጽሙ ላይ ተጠያቂነት የሚያስከትለውን ስምምነት በ1949 Ratify ስታደርግ ሕግን ልታስከበር ጥፋተኞችን ልትቀጣ ተስማምታለች። በ1950 ዎቹም ይህንኑ ስምምነት በቀጥታ ወደ ህጎቿ በማዋሃድ ወንጀሉንና ተጠያቂነቱን በ1957 ዓ.ም የወንጀለኛ መቅጫ ሕጎቿ ውስጥ አካታለች።

መንግስት መፍትሔ ሊሰጠን ካልቻለ። ግፍን፣ ጭካኔንና ጭፍጨፋን አንለምድም። ዝም አንለም ማለት አለብን። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያንም ኢትዮጵያ የፈረመችውንና ያጸደቀችውን የጂኖሳይድ ስምምነቶችን መሰረት በማድረግ የተባበሩት መንግስታት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያጸደቀውን ስምምነት እንዲያከብር፣ እንዲያስከብርና ሕጉን እንዲያስፈጽም አቤት ማለት አለባት።

እግዜአብሔር በአርሲ ለተጨፈጨፉ ኦርቶዶክሳውያን ጽድቅን ለቤተሰቦቻቸውና ለምዕመናን መጽናናትን እንዲሰጥ እመኛለሁ!!!


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: