የቻይናው ኩባንያ የአዲስአበባ አውቶቡሶችን ወደ ተፈጥሮ ጋዝ ተሽከርካሪዎች የመቀየር ሥራ ጀመረኢትዮጵያ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የቻይናው ኩባንያ የአዲስአበባ አውቶቡሶችን ወደ ተፈጥሮ ጋዝ ተሽከርካሪዎች የመቀየር ሥራ ጀመረ
ኢትዮጵያ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶችን ከናፍጣ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ ለመቀየር የሚያስችል መጠነ ሰፊ ፕሮግራም የጀመረች ሲሆን፥ በቻይናው ኩባንያ የመጀመሪያው ማሻሻያ የተደረገለት አውቶቡስ በአዲስ አበባ የጎዳና ላይ ፍተሻውን በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቁን ቻይና ዴይሊ ዘግቧል።
በቻይናው ጂሲኤል አፍሪካ ኢንዱስትሪያል ግሩፕ የሚመራው ይህ መርሃ ግብር፥ ኢትዮጵያ ከውጭ በሚገባ ነዳጅ ላይ ያላትን ጥገኝነት ለመቀነስ እና ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ የሆነ የሕዝብ ትራንስፖርትን ለማስፋፋት የምታደርገው ሰፊ ጥረት አካል ነው ተብሏል።
ቻይና ዴይሊ እንደዘገበው፤ ፕሮጀክቱ፤ በአዲስ አበባ አገልግሎት የሚሰጡ ከ2,000 በላይ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶችን በስምንት ወራት ውስጥ ለመቀየር ያለመ ነው።
በተጨማሪም የመንግሥት ንብረት የሆኑ የመርሴዲስ ቤንዝ አውቶቡሶችን ለመቀየር ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: