የአያቶላ አሊ ኻሜኒ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ከ4 ወራት በኋላ በሰኔ ወር ሊፈጸም ነው!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በመካከለኛው ምስራቅ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና እጅግ ግዙፍ የተባለለት የሽኝት ፕሮግራም ይፋ ሆኗል። ባለፈው የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም (የካቲት 28, 2026) በቴህራን በሚገኘው መኖሪያና ቢሯቸው ላይ በተሰነዘረ የጋራ የአሜሪካ እና የእስራኤል የአየር ጥቃት ከቤተሰቦቻቸው ጋር የተገደሉት የ86 ዓመቱ የኢራን የበላይ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኒ፣ ከናፈቁት የመጨረሻ ምኞታቸው ጋር በተያያዘ በማሽሃድ በሚገኘው ታዋቂው የኢማም ረዛ መቅደስ አጠገብ ሊቀበሩ መሆኑ ተረጋግጧል።

የኢራን አብዮታዊ ጠባቂ ጦር (IRGC) እንዳስታወቀው ታላቁ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በሰኔ 14 ቀን (June 21) አካባቢ የሚጀምር ሲሆን ለሦስት ቀናት የሚቆይና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢራናውያን የሚሳተፉበት አገር አቀፍ የሽኝት ሰልፍ በቴህራን፣ በቆም እና በማሽሃድ ከተሞች ላይ ይካሄዳል ተብሏል።

የሀገሪቱ ባለስልጣናት እንደገለጹት በዚህ ታሪካዊ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ላይ ከ20 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ሊታደም ይችላል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ይህም በሰው ልጅ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ትልቁ ህዝባዊ ስብስብ ያደርገዋል።

እንደ መናኸሪያ ኤፍ ኤም ዘገባ ይህ አስገራሚ የህዝብ ቁጥር እ.ኤ.አ በ1989 የተከናወነውን እና 10 ሚሊዮን ህዝብ የተገኘበትን የቀድሞውን መሪ የአያቶላ ሩሆላ ኾሜኒን የቀብር ሥነ-ሥርዓት በእጅጉ የሚበልጥ እንደሚሆን ተነግሯል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: