ሿሿ ሲሰሩ የተያዙት ሴቶች‼️
የሿሿ ወንጀል የፈጸሙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ሳሪስ አቦ የትራፊክ መብራት አካባቢ ነው።
ተጠርጣሪዎቹ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 A 02122 ኦሮ በሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪና ተጠቃሚ በመምሰል አዲሱ መኮንንና ኢሳያስ ደገፋ የተባሉ የግል ተበዳዮችን በመጫን ጥቂት እንደተጓዙ ኪሳቸው ውስጥ የነበረውን የሞባይል ስልክ እና ገንዘብ ለመውሰድ ሲሞክሩ የግል ተበዳዮች ወንጀሉን ለመከላከል በሚሞክሩበት ወቅት ገፍትረዋቸው በፍጥነት በመጓዝ ላይ ሳሉ ከሌላ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨት ቆመዋል።
በወቅቱ ድርጊቱን በተመለከተው የአካባቢው ህብረተሰብና በትራፊክ ፖሊስ አማካኝነት በተሽከርካሪው ውስጥ የነበሩ ትዕግስት ጌታቸው፣ ገነት ደሳለኝ፣ ሜላት ጌታቸው፣ እየሩሳሌም ጌታነህና መአዛ ማሞ የተባሉ ተጠርጣሪዎችን ከ6 የተለያዩ ስማርት ሞባይል ስልኮችና 11 ሚሞሪ ካርዶች ጋር ሊያዙ መቻላቸውን በወንጀል ምርመራ ም/ዋና ጠቅላይ መምሪያ የልዩ ልዩ እና የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በተያዙ ተጠርጣሪዎች ላይ ተገቢው ምርመራ የማስፋት ተግባር እየተከናወነ ሲሆን ሌሎች ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋልም ከፍተኛ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።
ተጠርጣሪዎቹ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እየተንቀሳቀሱ ወንጀሉን የሚፈፅሙ በመሆናቸው በእነዚህ ተጠርጣሪዎች ወንጀል የተፈጸመባቸው አዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በመቅረብ ስልኮቻቸውን መረከብ እንደሚችሉ ተገልጿል።
@Seledadotio

No comments yet.