አሜሪካ ቪዛ በፍጥነት ለማግኘት ለሚፈልጉ መንገደኞች የ750 ዶላር ተጨማሪ ክፍያ የሚጠይቅ አዲስ የሙከራ አሰራር ይፋ አደረገች …

- Advertisement -
Sidebar AD
አሜሪካ ቪዛ በፍጥነት ለማግኘት ለሚፈልጉ መንገደኞች የ750 ዶላር ተጨማሪ ክፍያ የሚጠይቅ አዲስ የሙከራ አሰራር ይፋ አደረገች
​የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሰኔ 24 ቀን እስከ ታኅሣሥ 22 ቀን 2019 ዓ.ም የሚቆይ አዲስ የቪዛ አገልግሎት መጀመሩን አስታውቋል።
ይህ አሰራር አመልካቾች ከመደበኛው 185 ዶላር በተጨማሪ 750 ዶላር በመክፈል በ10 ቀናት ውስጥ የቃለ መጠይቅ ቀጠሮ እንዲያገኙ ያስችላል።

አላማውም በትራምፕ አስተዳደር ጥብቅ የቪዛ ቁጥጥር (የማህበራዊ ሚዲያ ፍተሻ እና እስከ 15,000 ዶላር ዋስትና ማስያዝን ጨምሮ) የመጣውን ከፍተኛ የቀጠሮ መዘግየት መቀነስ ነው።
​ ነገር ግን ይህንን ፕሪሚየም ክፍያ መክፈል የቪዛ መፈቀድን በፍጹም አያረጋግጥም ተብሏል።
​አገልግሎቱ የሚሰጥባቸው የተመረጡ ኤምባሲዎች ዝርዝር በቅርቡ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: