ለቤተሰቦቿ መልዕክት ልታደርስ የሄደችውን ታዳጊ በመጥለፍ ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለመፈጸም ሙከራ ያደረገዉ ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ
በጌዴኦ ዞን ባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክልን በመጠቀም የጠለፋ እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለመፈፀም ሙከራ ያደረገዉ ተከሳሽ በእስራት መቀጣቱ ተገልጿል።
ተከሳሽ ዮሴፍ ምትኩ የተባለ ሲሆን የግል ተበዳይ ታዳጊ በረከት ተስፋዬ ለቤተሰቦቿ መልዕክት ልታደርስ ገበያ ስትሄድ ካልተያዙ ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን በያዙት ሞተር ሳይክል በመጠቀም የወንጀል ድርጊት መፈፀሙን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ሀይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በዚህም ፖሊስ ተከሳሽ ጥፋተኛ መሆኑን በማረጋገጥ በፈፀመው የጠለፋ ወንጀል እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ወንጀል ጥፋተኛ መሆኑን በማረገጥ ክስ መስርቶ ለወናጎ ወረዳ ፍርድ ቤት ያቀርባል።
ጉዳዩን የተመለከተዉ የወናጎ ወረዳ ፍርድ ቤት የቀረበለትን የክስ አቤቱታ ሲመረምር ቆይቶ ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ/ም በዋለዉ ችሎት ተከሳሹ በተከሰሰበት በሁለቱም ወንጀሎች ጥፋተኛ መሆኑን ፍርድ ቤቱ በማረጋገጥ ተከሳሽ ዮሴፍ ምትኩን በ9 ዓመት ከስምንት ወር እስር እንዲቀጣ ፍርድ ቤቱ መወሰኑን ኢንስፔክተር አሸናፊ ሀይሌ ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
@Seledadotio

No comments yet.