#FastMereja I ትናንት ምሽት በሜክሲኮ በተጀመረው የዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ፣ ሜክሲኮ ደቡብ አፍሪካን በመግጠም ውድድሩን በድል ጀምራለች። ጨዋታው በሜዳ ላይ ከነበረው ፉክክር ባሻገር፣ በሶሻል ሚዲያ መድረኮች ላይ ከፍተኛ ትኩረት የሳበ ክስተት ሆኗል።
የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን መሸነፉን ተከትሎ፣ በርካታ አፍሪካዊያን በሶሻል ሚዲያ መድረኮች ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። ይህ ስሜት የመነጨው በደቡብ አፍሪካ ውስጥ በሚኖሩ ሌሎች አፍሪካዊያን ስደተኞች ላይ በቅርቡ በተፈጠረው “ከሀገራችን ውጡልን” ጥሪ እና ተያያዥ ፀረ-ስደተኞች እንቅስቃሴ ሳቢያ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ።
በሶሻል ሚዲያ አስተያየት ሰጪዎች እንደገለጹት፣ የደቡብ አፍሪካ ቡድን መሸነፍ በወቅቱ በሀገሪቱ እየታየ ካለው የመገፋፋት ስሜት ጋር በተያያዘ፣ በሌሎች አፍሪካዊያን ዘንድ እንደ አንድ የምሬት መግለጫ እየታየ ነው።
Source: FastMereja









No comments yet.